Image

የደቡብ አፍሪካ ፀረ ስደተኞች እንቅስቃሴ መሪዎች ስደተኞች ከአገሪቱ እንዲወጡ ያስቀመጡት ቀነ ገደብ ነገ ጁን 30 ቀን 2026 እንደሚያበቃ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ይህንን ተከትሎ፤ በፕሪቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እራሳቸውን ከጥቃት እንዲጠብቁና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች እስከሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ጁን 30 ቀን 2018 ባለው ጊዜ ውስጥ አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ በፀረ ስደተኞች እንቅስቃሴ መሪዎች ቀነ ገደብ መቀመጡ ይታወሳል።

በሕገ ወጥ ስደተኞች ላይ እንደሚሠራ የሚገልጸው ‘ማርች ኤንድ ማርች’ የተሰኘው እንቅስቃሴ መሪ ጃሲንታ እንጎቤሴ ዙማ በሰጡት መግለጫ ይህ ቀነ ገደብ እንደተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል።

ጆሃንስበርግ እና ፕሪቶሪያ ውስጥ በንግድ ስራ ተሰማርቶ ለሰባት ዓመታት የቆየው ሰለሞን ግዛው የተባለ ኢትዮጵያዊ ለኢትዮ ፎከስ ዝግጅት ክፍል እንደተናገረው በደቡብ አፍሪካ  በተለይ ፕሪቶሪያ ውስጥ ዓለም በይፋ ያላወቀው “ኦሽዊትዝ ካምፕ” ተቋቁሞ ንጹሃን እየተጨፈጨፉበት ነው ብሏል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በተለይ የዙሉ ማህበረሰብ አባላት የሆኑ ወጣቶች ሀገራቸው በምን አይነት የቅኝ ግዛት መከራ ውስጥ እንዳለፈች መረጃ የላቸውም ወይም መስማት አይፈልጉም ያሉት አቶ ሰለሞን ዛሬ ጎራዴ አንስተው አንገታቸውን የሚቆርጧቸው ኢትዮጵያውያንና የምዕራብ አፍሪካ ዜጎች እነሱን ከቅኝ ግዛት ቀንበር እንዲላቀቁ ለማድረግ መስዋዕትነት ከከፈሉ ሃገራት የመጡ መሆናቸውን ሊያውቁ ይገባቸው ነበር ብለዋል፡፡

ሁኔታው በእጅጉ ያሳሰበው በፕሪቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሐሙስ ሰኔ 18 ቀን ባወጣው ማሳሰቢያ፤ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ሁኔታን አስመልክቶ “ከመንግሥት ጋር አስፈላጊውን ግንኙነት” እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

የደቡብ አፍሪካ መንግሥት “ስደተኞች ላይ የኃይል ጥቃት” እንዳይደርስ ጥበቃ እንደሚያደርግ ሲገልጽ መቆየቱን አስታውሶም፤ የአገሪቱ መንግሥት “በቀጣይ ቀናት የፀጥታ ማስከበር ተግባሩን እንደሚያጠናክር ይጠበቃል” ብሏል።

ይሁን እንጂ ስደተኞች ላይ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ያለውን ስጋት ገልጿል። “በስደተኞች ላይ ሕገ ወጥ ድርጊት እና ጥቃቶች ሊፈጸሙ የሚችሉበት ሁኔታዎች እንዳሉ የሚጠቁሙ አዝማሚያዎች አሁንም ይስተዋላሉ” ሲል በመግለጫው አስፍሯል።

“የመብት መጣስ እና የደኅንነት ስጋቶች” መኖራቸውን የገለጸው ኤምባሲው፤ በዚህም የተነሳ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች “የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችሁን ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ እንድታደርጉ” ሲል ዜጎቹን አሳስቧል።

በየአካባቢያቸው ከሚገኙ የመንግሥት አካላት እና የኮሚዩኒቲ አደረጃጀቶች ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲያደርጉም መክሯል። ከእነዚህ አካላት ጋር “መረጃ በመለዋወጥ ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ኤምባሲው ማሳሰቢያ ያቀርባል” ሲልም አስጠንቅቋል።

ኤምባሲው ከሁለት ወር በፊት በቀናት ልዩነት አራት ኢትዮጵያውያን መገደላቸው በተሰማበት ወቅት የአገሪቱ መንግሥት ግድያውን በተመለከተ “በአስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ” እና “ችግር በሚታይባቸው አካባቢዎች ልዩ ጥበቃ” እንዲያደርግ መጠየቁን አስታውቆ ነበር።

ኤምባሲው በወቅቱ ባወጣው መግለጫ ግድያዎቹ በደቡብ አፍሪካ ከሚታየው መጤ ጠልነት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችልም ገልጾ ነበር። ከዚያ ጊዜ በኋላ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚካሄዱ የፀረ ስደተኞች ሰልፎች ተበራክተዋል። የተለያዩ አገራት ስደተኞች ላይ ጥቃት ሲፈጸም ያሳያሉ የተባሉ ቪዲዮዎችም ተሠራጭተዋል።

በእነዚህ እንቅስቃሴዎች የተነሳ ስደተኞች ላይ ስጋት በመፈጠሩ ናይጄሪያ እና ጋና ዜጎቻቸውን ከደቡብ አፍሪካ አስወጥተዋል። የዚህ እንቅስቃሴ መሪዎች ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች ከደቡብ አፍሪካ እንዲወጡ ቀነ ገደብ በተቀመጠበት ጁን 30 ቀን ሰልፍ እንዲካሄድ አስታውቀዋል።

“ማንም ሰው ላይ ጉዳት ማድረስም ዓላማችን አይደለም። እኛ የምንጠይቀው ነገር ቢኖር ሕገ-ወጥ ስደተኞች አገራችንን ለቅቀው እንዲወጡ እና መንግሥት ቀድሞውኑ ያሉትን ሕጎች እንዲያስከብር ብቻ ነው” ሲሉ የማርች ኤንድ ማርች መሪ ተናግረዋል።

ይህ ለስደተኞች የተቀመጠው ቀነ ገደብ በአፍሪካ ሕብረት ስር ከሚገኘው እና የዳኝነት አካል ከሆነው የአፍሪካ የሰብአዊ እና ሰዎች መብቶች ኮሚሽን ትችት ቀርቦበታል። ኮሚሽኑ ትናንት ሐሙስ ባወጣው መግለጫ፤ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ የተደራጁ ቡድኖች “በሌሎች የአፍሪካ አገራት ዜጎች ላይ” ያስቀመጡት ቀነ ገደብ “ጥልቅ ስጋት” እንደተሰማው ገልጿል።

መግለጫው፤ “ኮሚሽኑ ኦፕሬሽን ዱዱላ እና ማርች-ማርች በተባሉ የተደራጁ ቡድኖች በተለይም ከሌሎች የአፍሪካ አገራት በመጡ ስደተኞች ላይ የሚፈጸሙትን የማስፈራራት፣ የጥቃት እና የኃይል እርምጃ ድርጊቶች አጥብቆ ያግዛል” ይላል።

ይህ አይነቱ ድርጊት በአፍሪካ የሰብአዊ እና ሰዎች መብቶች ቻርተር ላይ የተቀመጡ መሠረታዊ መብቶችን የሚጥስ እንደሆነም ኮሚሽኑ ገልጿል። ከስደተኞች ጋር የተያያዙ ሕጎችን የማስፈጸም ኃላፊነት “የተፈቀደላቸው የመንግሥት ተቋማት ብቻ” እንደሆነ ያስታወሰው ኮሚሽኑ፤ የአገሪቱ መንግሥት ለስደተኞች የሚያደርገው ጥበቃ እንዲያጠናክር ጠይቋል።

“በሕገ ወጥ የሕግ ማስፈጸም እንቅስቃሴዎች” ውስጥ የሚሳተፉ ቡድኖችን “ለመበተን እና ለመግታት ጠንካራ እርምጃ” እንዲወስድም አሳስቧል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026