Image

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶማስ ፒጎት እ.ኤ.አ ሰኔ 17 ቀን 2026 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እና ለመሠረት ሚድያ አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በኩል የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው እርምጃው የተወሰደው በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በማደናቀፍ ረገድ ቀጥተኛ ተሳትፎ ባላቸው ወይም ተባባሪ በሆኑ ግለሰቦች ላይ ነው።

የቃል አቀባዩ መግለጫ እንዳመለከተው በሕወሓት አመራሮች እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል በቅርቡ እያገረሸ የመጣው ውጥረት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

በዘንድሮው ዓመት መጀመሪያ ላይ የትግራይ ደኅንነት ኃይሎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር መጋጨታቸውን ያስታወሰው መግለጫው ይህም የ600 ሺህ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የ2020-2022ቱ ጦርነት ካበቃ ወዲህ በሁለቱ አካላት መካከል የተደረገ የመጀመሪያው ቀጥተኛ ወታደራዊ ፍልሚያ መሆኑን ገልጿል።

ይህን ተከትሎም በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ዜጎች ዳግም ወደ ጦርነት አዙሪት እንዳይመለሱ በመስጋት መኖሪያ ቀያቸውን ጥለው እየተሰደዱ መሆኑ ተመላክቷል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በሀገሪቱ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አዋጅ አንቀጽ 212(a)(3)(C) በተሰጣቸው ሕጋዊ ሥልጣን መሠረት እርምጃውን መውሰድ መጀመራቸውን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

“ይህ የቪዛ ገደብ ፖሊሲ በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በማደናቀፍ ረገድ ተጠያቂ የሆኑ ወይም እጃቸው ያለበትን የሕወሓት አክራሪ አቋም አራማጅ (hardline) አባላትን እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን ለይቶ የሚመለከት ነው” በማለት ቶማስ ፒጎት ተናግረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በሰላምና በክብር መኖር ከሚፈልገው የትግራይ ሕዝብን ጨምሮ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን መቆሟን እንደምትቀጥል መግለጫው ያረጋገጠ ሲሆን በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን አደጋ ላይ የሚጥሉ የሕወሓት ባለሥልጣናት እና ሌሎች ግለሰቦችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥና ድርጊታቸውን ይፋ ለማድረግ ዋሽንግተን ያሏትን ዲፕሎማሲያዊ መሣሪያዎች ሁሉ መጠቀም እንደምትቀጥል አስታውቃለች።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026