Image

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል የባዕዳን ተልእኮ የወሰዱ ያሏቸውን ታታቂዎች ተቹ፡፡ ርዕሰመስተዳድሩ እና ሌሎችም የክልሉ ባለስልጣናት በጨፌ ኦሮሚያ አባላት የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ችግሮች እልባትን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ “የተጠመዱ” ያሏቸውን የታጠቁ አማጺያንን የህዝብ ፍላጎት በመቃረን ከሰዋል፡፡

የምክር ቤቱ የፀጥታ ጥያቄዎች የስራ ዘመኑ የተጠናቀቀው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጬፌ ኦሮሚያ) ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምረው ዛሬ ባጠናቀቀው የጨፌው 6ኛ የስራ ዘመን 5ኛ ዓመት 11ኛው መደበኛ ጉባኤው፤ ትኩረት ሰጥቶት ከተወያየባቸው ጉዳዮች አንዱ የክልሉን ሰላምና ጸጥታን በተመለከተ ነው፡፡

ተሰናባች የምክር ቤቱ አባላት ከዚሁ ጋር ተያይዞ ባነሱት ጥያቄም፤ “ሰላም እና ጸጥታን በተመለከተ የክልላችን ህዝብ እና መንግስት እስካሁን የሰሩት ስራ እውቅና የሚሰጠው ቢሆንም፤ ይህ ችግር ከመሰረቱ ሊፈታ አልቻለም፡፡ በዚህ ላይ መስራት እጅግ ወሳኝ ነው” ያሉት አንድ የምክር ቤቱ አባል ሌላም ጥያቄ ተመሳሳይ ጥያቄ ተከትሏቸው፤ “በተለየ መንገድ ሰርተን የኦሮሞን ቀዬ ዘላቂ ሰላም የሰፈነበት ለማድረግ በ2019 በጀት ዓመት ምን ታቅዷል” የሚል ነው፡፡

በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ አቶ ከፍያለው ተፈራ ለእነዚህ የምክር ቤቱ አባላት ሰላምን ፀጥታን በተመለከተ ባነሱዋቸው ጥያቄዎች ላይ በሰጡት ቀጥተኛ ምላሽ፤ “ኦሮምኛ ተናጋሪ እና አማርኛ ተናጋሪ ሸነዎች የተለያዩ ችግሮችን ለመፍጠር ጥረት እያደረጉ ነው፡፡

ሁለቱም አካላት አብሮ ሊሄድ የሚችል አንድም እቅድ የላቸውም፤ ከሌላ አካል ነው ተልእኮ ወስደው የሚሰሩት፤ ፍላጎታቸው የተጀመረውን ልማት ማፍረስ፣ መንግስታዊ ስርዓት መናድ ነው፤ የሚከፈለውን መስዋእትነት ሁሉ ከፍለን ይህ ተልእኳቸው እንዲከሽፍ ወደፊትም አጠናክረን የምንሰራበት ይሆናል” ብለዋል፡፡ 

አቶ ከፍያለው በማብራሪያቸው ወቅት “አማርኛ እና ኦሮምኛ ተናጋሪ ሸኔ” ያሏቸውን በስም ባይጠቅሱም በተለያዩ ጊዜያት በክልሉ ውስጥ መንግስትን በትጥቅ የሚወጉ መንግስት ሸነ የሚሏቸው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በክልሉ የምስራቅ ወለጋ እና ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞኖች አዋሳኝ አከባቢዎች ላይ መንግስት ጥቃት በማድረስ የሚከሳቸው የፋኖ ታጣቂዎች ናቸው የሚል ግንዛቤ ግን ይያዝበታል፡፡ 

አቶ ከፍያለው ሰላምን በሰላማዊ መንገድ ለማምጣት ተደርጓል ባሉት ጥረትም በኦሮሚያ በርካታ ታጣቂዎች ወደ ሰላም መመለሳቸውን ጠቅሰው ከነዚህ ውስጥ ከሰባት ሺህ ባላይ ለሚሆኑ የታድሶ ስልጠና ተሰቷቸው የስራ እድልም እንደተፈጠረላቸው ነው የገለጹት፡፡

የክልሉን የ2018 በጀት አመት አፈጻጸም እና 2019 ዓ.ም እቅድን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በፊናቸው፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በክልሉ ጠንካራ ያሉት መረጋጋት መምታቱን አብራርተዋል፡፡ አቶ ሽመልስ በክልሉ ተስተዋለ ባሉት “መረጋጋት” የክልሉ ማህበረሰብ ኑሮም እንዲሻሻል አስተዋጽኦ አድርጓል ሲሉ ነው የተደመጡት፡፡

ተሰናባቾቹ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ባለፉት አምስት ዓመታት ችግሮችን ነቅሰው በማውጣት “መረጋጋት እንዲፈጠር” ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ያሏቸውን ያመሰገኑት ሽመልስ፤ ለሚቀጥሉት ዓመታትም መሰረት መጣሉን ነው የገለጹት፡፡ ያም ሆኖ ግን የክልሉን ህዝብ ትግልና ጥቅም የሚጎዱ በርካታ ሸፍጦች ተሸርበው ብርቱ ፈተናን ስደቅኑ መቆታቸውንም ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡

“ከምርጫ 2013 ወዲህ በዚህ አገር ያልተከሰተ ምን አለ” ብለው የጤቁት ርዕወሰመስተዳድሩ፤ “ይህ ህዝብ ግን ችግሮችን የመቋቋም አቅሙ ድንቅ በመሆኑ ብቻ አገሩን እየቀየረ እዚህ ደርሷል” ሲሉም የክልሉን ነዋሪዎች በአድናቆት አሞካሽተዋል፡፡ “የዚህን ህዝብ አቅም ያልተረዱ ወገኖች የተለያዩ ፍላጎቶችን ያሳያሉ፤ የተጠመዱ ሰዎች፤ ስጠመዱ ለበዓዳ ለማረስ ነው በተቃርኖ እርሰበርሳቸው የተጠመዱት፤ አንዱ ወደ ምስራቅ ሌላው ወደ ምዕራብ ነው የተጠመደው፡፡

እነዚህ ናቸው ደግሞ ስለ ኦሮሞ ህዝብ ትግል ጠበቃ ለመሆንና ችግር ገጥሞታል እያሉ ቅሬታ ለማቅረብ የሚቃጣቸው፡፡ ኦሮሞ እና ኦሮሚያን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሱት ጋር ተጠግተው ነው ወዲህ ዞረው ደግሞ ጅብ በማያውቀት አገር የሚባለውን ተረት የሚያስተርቱ፡፡ ለአጭር ጊዜ ፖለቲካዊ ፍላጎት ሁሉንም አይነት ሸፍጥ ብሰሩም ህዝባችን ያውቃቸዋል፡፡

የኦሮሞ ህዝብም ሆነ የክልሉ መንግስት የማንም ሀቅ አይፈልጉም፡፡ ለሀቃችን ግን አንገታችንን እንሰጣለን፡፡ ህዝብችንም ይታገላቸዋል፡፡ የኛም ተላላኪዎች አብረው ይቀላሉ እንጂ በፍጹም ዳግም ባርነት አይታሰብም፡፡ በቀያችን በሀቅ ከማንም ጋር ለመኖር ግን ዝግጁ ነን” ብለዋልም፡፡

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026