Image

የባሕር ላይ ፈንጂዎችና ድሮኖችን ጨምሮ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎን ታጠቁት የየመን ሁቲዎች ለኢትዮጵያ ቅርብ በሆነው የቀይባህር ክፍል ላይ የነዳጅም ሆኑ ሌሎች የጭነት መርከቦች እንዳይተላለፉ እገዳ መጣላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በመዝጋቷ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ የመርከቦች እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና ተፈጥሯል። አጋሮቿ ደግሞ በቀይ ባሕር በኩል ሌላ ግንባር ለመክፈት ሲዝቱ ቆይተዋል።

አሁን ሰሜናዊ የመንን የሚቆጣጠሩት እና በኢራን የሚደገፉት ሁቲዎች የዓለም 12 በመቶው የነዳጅ ፍጆታ የሚጓጓዝበት ወደ ቀይ ባሕር በሚያስገባው የባብ ኤል መንደብ ወሳኝ የባሕር መተላለፊያ በኩል የአሜሪካ ወዳጅ የሆነችው የሳዑዲ አረቢያ መርከቦች እንዳያልፉ ዕገዳ ጥለዋል።

ሐምሌ13/2018 ዓ.ም የሁቲ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሪ እንደተናገሩት በመርከቦቿ ላይ ዕቀባው የተጣለው ሁቲዎች በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች በሚገኙ ወደቦች እና የአውሮፕላን ማረፊያዎች ላይ ሳዑዲ ለጣለችው ዕገዳ አጸፋ ነው።

በምላሹም የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክሱን አውግዞ አገሪቱ “በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የመርከቦቿን ለመከላከል አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃዎችን ትወስዳለች” በማለት ዝቷል።

ሁቲዎች ከአስር ዓመት በፊት በሰነዓ የነበረውን የአገሪቱን መንግሥት ካስወገዱ በኋላ የመን በእርስ በርስ ጦርነት ወድማለች። የየመንን መንግሥት ወደ ሥልጣን ለመመለስ በሳዑዲ የሚመራው የአረብ አገራት ጥምረት ጣልቃ በመግባቱ ግጭቱ ተባብሷል።

አስራ ሁለት ዓመታት ባስቆጠረው ጦርነት ከ150 ሺህ በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ በተባበሩት መንግሥታት ግምት መሠረት ከ22 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለእርዳታ ፈላጊነት ያጋለጠ በዓለም ከሚጠቀሱ የሰብአዊ ቀውሶች አንዱ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል።

ሁቲዎች ከሳዑዲ ወደቦች የሚነሱ እና ወደ ሳዑዲ የሚያመሩ መርከቦች በደቡባዊ ቀይ ባሕር በኩል እንዳያልፉ በማገዳቸው በርካታ መርከቦች አቅጣጫቸውን ለመቀየር ተገድደዋል።

መቀመጫውን ለንደን ባደረጋው የቻተም ሐውስ የባለሙያዎች ስብስብ ውስጥ የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ባለሙያ የሆኑት ፋራይ ኤል-ሙስሊሚ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሁቲዎች የባሕር ላይ እንቅስቃሴውን ለማደናቀፍ የጦር መሳሪያ አቅሙ አላቸው።

“ሁቲዎች የባሕር ላይ ፈንጂዎች ያሏቸው ሲሆን፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የባሕር ላይ ድሮኖች የመጠቀም አቅማቸውን አሳድገዋል” ብለዋል። ስለዚህም በቀይ ባሕር ላይ የእንቅስቃሴ እገዳ ሳይጥሉ በአካባቢው ችግር የመፍጠር አቅም አላቸው።

ሙስሊሚ እንደሚሉት ሁቲዎች ቀውሱን ለመፍጠር ማድረግ ያለባቸው “አንድ ዒላማ ብቻ መምታት ነው። ምንም እንኳን ማሳያ ቢሆንም በኢንሹራንስ፣ በመርከብ እና በነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች ላይ ፍርሃትን ይፈጥራል። ይህም ሰዎች ከሚያስቡት በላይ ከፍተኛ ጉዳትን ያስከትላል።

“ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የኢራን ስትራቴጂ ደግሞ በቀጣናው ያሉ የአሜሪካ አጋሮች እንዲጎዱ ማድረግ ነው። ሁሉም ወደ ጦርነቱ እንዲገቡ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው።” ቀደም ሲል ኢራን “ሌላ ግንባር እንደምትከፍት” ስታስፈራራ የነበረ ሲሆን፣ የየመን ጉዳዮች ባለሙያ የሆኑት አንዋት አል-አንሲ እንደሚሉት ደግሞ ሁቲዎች የኢራንን ፍላጎት ለማሳካት ሳዑዲ አረቢያን ወደ ግጭቱ ለመሳብ እየጣሩ ነው።

“ኢራን ያላት ብቸኛው አማራጭ በመሆኑ ይህ ሁኔታ የበለጠ መካረሩን ትፈልገዋለች። ሳዑዲዎች ከኢራን ጋር መጋፈጥን ሲያርቁት የቆዩ ቢሆንም፣ ሁቲዎች የሚያጠቁ ከሆነ ጥቅማቸውን ለማስከበር እርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል” ብለዋል አንሲ።

“የባብ ኤል-መንዳብ ወሽመጥ ከዓለም ስትራቴጂካዊ የባሕር ወሽመጦች አንዱ እንደሆነ ይቆጠራል። ኢራን በወሽመጡ ላይ ስጋት የመደቀን ፍላጎትም ሆነ ችሎታ አላት” ሲሉ ከእስላማዊው አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያላቸው ወታደራዊ መኮንን መናገራቸውን ታስኒም የተባለው የኢራን ዜና ወኪል ከሳምንታት በፊት ዘግቦ ነበረ።

በባብ ኤል-መንደብ ወሽመጥ ላይ የሚሰነዘረው ማንኛውም ጥቃት በኢራን በሚደገፈው እና መቀመጫውን በየመን ባደረገው በሁቲ በኩል ሊሆን ይችላል። ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ አንድ የሁቲ መሪ ቡድኑ ቴህራንን በመደገፍ የባብ አል-መንደብ ወሽመጥን ለማጥቃት “በወታደራዊ መንገድ ዝግጁ” መሆኑን ለሮይተርስ ተናግሯል።

አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ ከአንድ ወር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁቲዎች ከቀናት በፊት እስራኤል ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። እስራኤል ከየመን የተሰነዘሩባትን ሁለት ሚሳዔሎችን እንደተኮሰች ተናግራለች።

ቡድኑ የየመንን የቀይ ባሕር ዳርቻዎች የሚቆጣጠር ሲሆን፣ በጋዛ ጦርነት ወቅት የባብ አል-መንደብ ወሽመጥን ዒላማ አድርጎ ነበር። ሁቲዎች ከ100 በላይ የንግድ መርከቦችን በሚሳዔል እና በድሮን አጥቅተው ሁለት መርከቦችን ያሰመጡ ሲሆን፣ አራት መርከበኞችን ገድለዋል።

 

 

ከስጋት ነጻ ሊሆን ያልቻለው ባብ አል-መንደብ በአረብኛ “የእምባ በር” ወይም “የሐዘን በር” እንደማለት ነው። በአካባቢው የሚከሰቱትን ከጠንካራ ወጀብ እና ሊተነብይ ከማይችል ነፋስ እስከ የባሕር ላይ ወንበዴዎች እንዲሁም ግጭትን የመሳሰሉ አደጋዎችን ለተመለከተ ስሙ አካባቢውን ይገልጸዋል።

ከ2008 እስከ 2012 ባለው ጊዜ ውስጥ የባብ አል-መንደብ ወሽመጥ እና በዙሪያው ያለው ውሃ በርካታ የባሕር ወንበዴ ጥቃቶችን አስተናግዷል። በዋናነት ጥቃቱ የሚፈጸመው በሶማሊያ ቡድኖች ሲሆን የመርከብ ሠራተኞችን አፍነው ገንዘብ ይጠይቃሉ። ክስተቶቹ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የመርከብ ኩባንያዎች በአካባቢው ያለውን ደኅንነት እንዲያጠናክሩ አስገድዷቸዋል።

የባሕር መስመሩ መዘጋት በሆርሙዝ ወሽመጥ ምክንያት የተዳከመውን የዓለም የነዳጅ እና የጋዝ አቅርቦትን የበለጠ በማወሳሰብ የዋጋ ንረቱን ያባብሰዋል። በባሕረ ሰላጤው የተፈጠረው የመርከብ ጉዞ መስተጓጎል የብሬንት ድፍድ ነዳጅ ዋጋ ከጦርነቱ በፊት ከነበረበት 70 ዶላር ወደ ከ115 ዶላር በላይ እንዲደርስ አድርጎታል።

ከሸማቾች ምርቶች እስከ ግብርና ሸቀጦች ድረስ ያለው ዓለም አቀፍ ንግድም ተጽዕኖው እየደረሰው ነው። በሌላ የባሕር መስመር ላይ አዲስ መስተጓጎል መፈጠሩ ዋጋዎችን የበለጠ ከፍ ሊያደርግ እና በኢራን ጦርነት የተፈጠረውን የኢኮኖሚ ውድቀት ሊያባብሰው ይችላል።

መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የባሕር ላይ እንቅስቃሴ ስጋቶች አማካሪ ተቋም ከሆነው ‘ባሻ ሪፖርት’ ሞሐመድ አልባሻ እንዳሉት ሁቲዎች ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚያቀኑ መርከቦችን ዒላማ ማድረግ ሊጀምሩ የሚችሉበት ሁኔታ ስለመኖሬ ግልጽ አይደለም።

“ምንም እንኳን መርከቦች ላይ ጥቃት ባይፈጸምባቸውም የሰጡት ማስጠንቀቂያ ብቻውን የመርከቦች እንቅስቃሴን በማደናቀፍ በተወሰኑ የሳዑዲ ወደ ቦች ላይ ስጋትን ሊፈጥር ይችላል። ስለዚህም ሁቲዎች ከማስፈራራት ወደ ቀጥተኛ ጥቃት የሚሸጋገሩ ከሆነ አሳሳቢ ይሆናል” በማለት አልባሻ ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026