Image

ሱዳን አገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ለመምጣቱ ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ከኢትዮጵያ ይገባ የነበረው የኃይል አቅርቦት መቋረጡ መሆኑን ሱዳን ትሪቡን የሀገሪቱን የኢነርጂ እና ነዳጅ ሚኒስቴር መግለጫ ጠቅሶ ዘግቧል።

አሁን ሱዳን ለገጠማት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ኢትዮጵያን ተጠያቂ አድርጋለች፡፡ የሱዳን የኢነርጂ ሚኒስቴር እንደሚለው በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች በቀን ከ18 ሰዓታት በላይ የሚደርሰ የኃይል መቋረጥ የተከሰተው ከኢትዮጵያ ከሚነሳው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በኩል ይቀርብ የነበረው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምክንያት ነው ብሏል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያቀረበው ሌላ ምክንያት ደግሞ በክረምት ወቅት የኤሌክትሪክ ፍላጎት በመጨመሩ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀደመ መኖሪያቸው መመለሳቸውን ተከተሎ የኃይል አጠቃቀም በማደጉ፣ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ኤሌክትሪክ ፍላጎት በመጨመሩ፣ በዋና ዋና የኃይል ማመንጫዎች ላይ የጥገና ሥራዎች እየተሰሩ በመሆኑ፣ የነዳጅ እና የመለዋወጫ ዕቃዎች እጥረት በመኖሩ ነው በማለት ህዝቡን ለማረጋጋት እየሞከረ መሆኑን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም፤ በኃይል ማመንጫዎች፣ በሰብስቴሽኖች እና በኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በተፈጸመ ውድመት፣ ስርቆት እና ስልታዊ ጥቃት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ የሀገሪቱን የኃይል መስመር የበለጠ አዳክሞታል ሲል ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የሱዳን ባለስልጣናት ይህንን ምክንያት በደረድሩም ሱዳን ከኢትዮጵያ በየቀኑ ታገኝ የነበረው 200 ጊጋ ባይት የኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠው መንግስታቸው ለኢትዮጵያ መክፈል የነበረበትን ክፍያ ለሶስት ተከታታይ አመታት ሳይከፍል በመቅረቱ ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡

በነሐሴ 2024 ዓ.ም የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፤ ሱዳን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የኤሌክትሪክ ክፍያ መክፈል ባለመቻሏ ያለባት ዕዳ ከ90 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሻግሯል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ሱዳን ለሦስት ዓመታት የኤሌክትሪክ ኃይል ክፍያ አልፈጸመችም ሲሉ ለፓርላማ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግን ተቋሙ በጦርነት ለተጎዳችው ሱዳን የኃይል አቅርቦቱን ለመቀጠል እቅድ እንዳለው መግለጻቸው ይታወሳል። በዚህ ጉዳይ ላይ ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየት የሰጡት አቶ ክብረት አሰፋ የተባሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጫችን እንደነገሩን ሱዳን 90 ሚሊዬን ዶላር ያልተከፈለ የኢትዮጵያ የማብራት ክፍያ እዳ አለባት።

ሱዳን ኢትጵያ ላይ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳት ለማድረስ ከሚንቀሳቀሱ ሀገራ ጋር ከመወገን ይልቅ በመልካም ጉርብትና ገለልተኛ አቋም ቢኖራት ኢትዮጵያም ይህንን እዳ ታግሳ ማቆየት ትችል ነበር ያሉት አቶ ክብረት ለተደጋጋሚ ጊዜያት የግብጽን ጬኸት ተቀብላ በህዳሴ ግድብ ላይ የተለመደ የውሸት ፕሮፓጋንዳዋን እየነዛች ትገኛለች። አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ስለተቋረጠብኝ ማብራት አጠረኝ ብላ ታላዝናለች ብለዋል።

የሱዳን ባለስልጣናት በኤልትሪክ ኃል እጥረት ምክንያት በህዝቡ ዘንድ የተቀሰቀሰውን ቁጣ ለማለዘብ የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው፣ የሱዳን ባለሥልጣናት በጥገና ሥራዎች አማካይነት ከ260 ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል መመለስ መቻሉን እና አሁን በመከናወን ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ያለው የማመንጨት አቅም ከ600 ሜጋዋት በላይ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አክሎም ከ20 በላይ ጉዳት የደረሰባቸው ሰብስቴሽኖች ዳግም ወደ ሥራ መመለሳቸውን እና የኢንጂነሪንግ ቡድኖች የጸጥታና የሎጂስቲክስ ፈተናዎች ቢኖሩባቸውም ከ1,700 ኪሎሜትር በላይ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን መጠገን መቻላቸውን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በሰጠው ማስተባበያ የማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና ትራንስፎርመሮችን የማቋቋም ሥራ መቀጠሉንና ሙሉ የማመንጨት አቅሙ እስኪመለስ ድረስ የኃይል መቆራረጥ እንደሚኖር አስታውቋል።

ይህ የተገለጸው ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ንግድን ለማመቻቸት ያለመ መሠረተ ልማት ግንባታ ማጠናቀቋን በቅርቡ ማስታወቋን ተከትሎ ነው። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፤ ፕሮጀክቱ መጠናቀቁን በአዲስ አበባ በተካሄደው 37ኛው የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ስቲሪንግ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ ላይ መግለጹ ተዘግቧል። በስብሰባው ላይ አባል ሀገራት ቀጠናዊ የኃይል ትስስር አስተዳደር ማሻሻያዎችን ለመተግበር ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ገበያ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንደገለጹት የመሠረተ ልማቱ መጠናቀቅ የድንበር ተሻጋሪ የኃይል ንግድን በማስፋፋት እና የኢነርጂ ትብብርን በማጠናከር በቀጠናው ያለውን የኤሌክትሪክ እጥረት ለመቅረፍ የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ ተናግረዋል።

ከሱዳን ጋር ባለው የኃይል ንግድ ቀጣይነት ዙሪያ ከዚህ ቀደም የተሰጡ ማረጋገጫዎች እያሉ ነው ከኢትዮጵያ የሚላከው የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ የተሰማው። በነሐሴ 2024 የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፤ ሱዳን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የኤሌክትሪክ ክፍያ መክፈል ባለመቻሏ ያለባት ዕዳ ከ90 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሻግሯል።

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ሱዳን ለሦስት ዓመታት የኤሌክትሪክ ኃይል ክፍያ አልፈጸመችም ሲሉ ለፓርላማ ተናግረዋል። የኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግን ተቋሙ በጦርነት ለተጎዳችው ሱዳን የኃይል አቅርቦቱን ለመቀጠል እቅድ እንዳለው መግለጻቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ቀጠናዊ የኤሌክትሪክ ኤክስፖርት ስትራቴጂዋን እያስፋፋች እንደምትገኝ ቀደም ሲል ተዘግቧል። በጥቅምት 2023 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያለፈው በጀት ዓመት ለሱዳን፣ ለኬንያ እና ለጂቡቲ 1,701 ጊጋዋት ሰዓት ማቅረቡን ተከትሎ የኤሌክትሪክ ኤክስፖርቱን ለማሳደግ ማቀዱን አስታውቆ ነበር፤ ይህም ዕቅድ 2,993 ጊጋ ዋት ሰዓት ኤክስፖርት በማድረግ 182 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ያለመ ነው።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026