Image

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሁነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ባጫ ደበሌ የሥራ ዘመናቸውን በማጠናቀቃቸው ምክንያት ወደ ሃገራቸው ሊመለሱ መሆኑ ተሰማ። ጀነራሉ ይህን አስመልክቶ ባለፈው ቅዳሜ የሽኝት መርሐ ግብር እንደተደረገላቸው በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

በኬንያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የናይሮቢ ቢሮ ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም እንዲሁም በመንግስታቱ ሀቢታት ተቋም የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ጀነራል ባጫ፣ በኬንያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሁነው ከመሾማቸው በፊት በመከላከያ ሰራዊት ዉስጥ ከፍተኛ አመራር የነበሩ እና በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ጡረታ ከወጡበት ወደ ሰራዊቱ መመለሳቸው እና ጦርነቱ ወደመጨረሻው ላይ ሲደርስ መሾማቸው የሚታወስ ነው።

ጀኔራሉ አሁን ላይ የአገልግሎት ጊዜያቸውን እንደጨረሱ ቢነገርም ሀገር ቤት መጥተው ሹመት ይጠብቃቸዋል፣ አይጠብቃቸውም የሚለውን በተመለከተ እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም።

ባጫ ደበሌ በሽኝት መርሃ-ግብራቸው ላይ ንግግር ሲያደርጉ በስራ ዘመናቸው በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል የነበረው ሁለንተናዊ ትስስር ወደ ላቀ የስትራቴጂክ አጋርነት እንዳሸተሻገረ መግለጻቸውን ኤምባሲው አስታውቋል።

አምባሳደሩ አክለውም “ሁለቱ እህትማማች” አገራት በሰላምና ደኅንነት ትብብር በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ጠቅሰው፣ በቆይታቸው የተፈረመው የመከላከያ ትብብር ስምምነት የትብብሩ ዋነኛ ማሳያ መሆኑን እንደገለፁ ታውቋል።

ጀነራሉ አክለውም በሁለቱ አገራት ባሉ የደህንነት መዋቅሮች መካከል በተፈጠረው የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ በመደረጉ “ኦነግ ሸኔ እና አል-ሸባብ ያሉ ጸረ-ሰላም ኃይሎችን” ከጋራ የድንበር አካባቢዎች ላይ በስኬት ማጽዳት ተችሏል ሲሉ ገልጸዋል።

እንዲሁም አምባሰደሩ በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ በተገኙት የአፍሪካ አምባሳደሮች እና ከፍተኛ ኮሚሽነር ሊቀመንበር ሌተናንት ፒተር ካኮዎ ላቫሁን፣ አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌን በቆይታቸው ከተሰጣቸው የአገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም ከማስከበር ተልዕኮ ባሻገር “የአፍሪካን የጋራ ጥቅም” እና አቋም “በጽናት ለማስከበር” የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች ጋር በመሆን ያከናወኑት ጠንካራ ተግባር ሁሌም ይታወሳል በማለት እንዳወደሷቸው ኤምባሲው ገልጿል።

አክሎም ጄኔራሉ አክለውም ለኬንያ መንግስት እና ለመላው የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ፣ የዲያስፖራ ማህበረሰብ እንዲሁም ከኤምባሲው ሠራተኞች ጋር ያሳለፉትን ስኬታማ የሥራ ዘመን በማውሳት አመስግነው ተሰናብተዋል ብሏል።

በፕሮግራሙ ላይ የኬንያ ውጭ ጉዳይ እና ዲያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴዔታ፣ በመወከል በኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር፣ በናይሮቢ የአፍሪካ አምባሳደሮች እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮች እንዲሁም ከ50 በላይ አገራት አምባሳደሮች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኬንያ መንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በኬንያ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ፣ በኬንያ የኢትዮጵያ ወዳጆች መገኘታቸውን ኤምባሲው አስታውቋል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026