Image

ህወሓት በአፋር እና በአማራ ክልሎች በሚገኙ የመንግስት ይዞታዎች ላይ አዲስ ጥቃት መክፈቱና በትግራይ የሚገኙ ኤርፖርቶችን መቆጣጠሩን የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ጌታቸው ረዳ አስታወቁ፡የጠቅላይ ሚኒስተሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች  አማካሪ እና የቀድሞው የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ፤ ህወሓት በአፋር እና በአማራ ክልሎች አዲስ ጥቃት መክፈቱና በትግራይ የሚገኙ ኤርፖርቶችን መቆጣጠሩን ተናግረዋል፡፡

 በይፋዊ ማህበራዊ ተስስር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ከሆነ፤ ህወሓት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብን ጨምሮ በርካታ አካላት በትግራይ ክልል ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ያደረጉትን ጥረት ወደ ጎን ትቷል በማለት  ዛሬ ማለዳ ላይ በአፋር እና በአማራ ክልሎች በሚገኙ የመንግስት ይዞታዎች ላይ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት ከፍቷል ብለዋል።

 ከዚሁ ጥቃት ጋር ተያይዞ ህወሓት በትግራይ ክልል በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር የነበሩ ኤርፖርቶችን ተቆጣጥሯል ያሉት ጌታቸው ይህም ወደ ክልሉ የሚደረጉና ከክልሉ የሚወጡ የበረራ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጡ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

የህወሓት ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራሮች የወሰዱት ይህ እርምጃ “ሀላፊነት የጎደለው ድርጊት” ነውም ብለዋል። ጌታቸው ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ የፌደራል መንግስት  የህወሓት ትንኮሳዎችን በመቋቋም ትዕግስት ላይ እንደነበር መግለፃቸው ይታወሳል። ሆኖም ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልል ግጭት ከጀመረ ከቁጥጥር ውጭ የሚሆን ጦርነት ሊነሳ ይችላል በማለትም አስጠንቅቀው ነበር።
 ለወራት በውጥረት ውስጥ በቆየው የትግራይ ክልል ውስጥ ግጭት መቀስቀሱን የህወሓት እና የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት መካከል ጦርነት መቀስቀሱ የተገለጸው ረቡዕ መስከረም 13/2019 ዓ.ም ማለዳ የትግራይ ኃይሎች መቀለ የሚገኘውን አውሮፕላን ማረፊያ ተቆጣጥረው በረራዎች መቋረጣቸው ከተነገረ በኋላ ነው።

የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን እና የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባጋሩት ጽሑፍ የህወሓት ኃይሎች ጦርነት መክፈታቸውን ገልጸዋል።

ትግራይን የሚያስተዳድሩት የህወሓት መሪዎች በበኩላቸው ባወጡት መግለጫ፤ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተከፈተብን ያሉትን ጥቃት ለመከላከል ኃይሎቻቸው እርምጃ እንዲወስዱ መታዘዛቸውን ገልጸዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪው አቶ ጌታቸው እንዳሉት “በትግራይ ሌላ ዙር ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ብዙዎች ጥረት ቢያደርጉም፣ ዛሬ ጠዋት የህወሓት አመራር” ጦርነት መክፈቱን አመለክተዋል።

አክለውም የህወሓት ኃይሎች በአፋር እና በአማራ ክልሎች በሚገኙ ቦታዎች በኩል ሙሉ ጥቃት መክፈታቸውን በመግለጽ ጦርነት መቀስቀሱ “እጅግ የሚያሳዝን” ክስተት ነው ብለዋል።

የህወሓት መሪዎች በበኩላቸው ኃይሎቻቸው ወደ መከላከል ውጊያ እርምጃ መግባታቸውን ገልጸው፤ ውሳኔው የተላለፈው የመንግሥት ኃይሎች ቀደም ብለው ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ነው ሲሉ ከስሰዋል።

የህወሓት አመራሮች የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥትን በማፍረስ ሥልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው የቆዩ ሲሆን፣ አልፎ አልፎም ግጭቶች ሲከሰቱ ነበር።

ውጥረቱ ወደ ቀጥተኛ ወታደራዊ ግጭት የተሸጋገረው የትግራይ ኃይሎች የመቀለውን አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያን ተቆጥጥረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎችን ማቋረጡን ካስታወቀ በኋላ ነው።

የትግራይ ኃይሎች ግጭቱን መቀስቀሳቸውን በኤክስ ገጻቸው ላይ ያመለከቱት አቶ ጌታቸው “የህወሓት የፖለቲካ እና የወታደራዊ አመራር ኃላፊነት የጎደለው አካሄድ ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን” ጠቅሰዋል።

ፌዴራል መንግስት የጦርነቱን መቀስቀስ አስመልክቶ እስካሁን በይፋ መግለጫ ያልሰጠ ሲሆን ህወሓት ግን ከጥቂት ሰዓታት በፊት ባወጣም መግለጫ በሰሜኑ ጦርነት እንዳደረገው ሁሉ ዛሬም “ወረራ ተፈፀመብኝ” ሲል ክስ አቅርቧል፡፡

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026