የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን አስታወቀ።
አየር መንገዱ ደንበኞቹ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ በመሄድ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከሉ 6787 በመደወል የጉዞ ምዝገባ ማስያዝ እንደሚችሉም ገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ክልል በነበረው “ወቅታዊ ሁኔታ” ምክንያት ከመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መቀሌ፣ አክሱምና ሽሬ የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለጊዜው ማቋረጡ ይታወቃል።
አየር መንገዱ በወቅቱ ባወጣው መግለጫ፣ የበረራ መቋረጡ ወደ ሶስቱ መድረሻዎች በሚደረጉ በረራዎች ላይ እንደሚተገበር ገልጾ “በበረራዎቹ መቋረጥ ምክንያት በደንበኞቻችን ላይ ለሚደርሰው መጉላላትም ከወዲሁ ይቅርታ እንጠይቃለን” በማለት ገልጿል።
አየር መንገዱ በወቅቱ ባወጣው መግለጫ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደ መቀሌ፣ አክሱም እና ሽሬ የሚያደርገውን በረራ ከዛሬ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለጊዜው አቋርጧል ” ሲል አስታውቋል።
በጸጥታና በአየር መንገድ ዘርፍ ያሉ የመረጃ ምንጮች በጊዜው ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች በመቀሌ የሚገኘውን የአሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን “በቁጥጥር ስር ያዋሉ” ሲሆን፣ የጸጥታ ኃይሎች ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በአየር ማረፊያው ዙሪያ ተሰማርተው ታይተዋል። በኋላ ለይ የመከላከያ ሰራዊት እና አጋር ኃይሎች አየር መንገዱን እና መቀሌ ከተማን ተቆጣጥረዋል።
የበረራ ስረዛው የተከሰተው የሰባት የኢትዮጵያ ተቃዋሚና የታጠቁ ቡድኖች አዲስ ጥምረት ማቋቋማቸውን ካስታወቁ በኋላ በትግራይ ውስጥ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ሲሆን ቡድኖቹ የብልጽግና ፓርቲ የሚመራውን መንግሥት ማስወገድ እና ሁሉንም ያካተተ የሽግግር መንግስት ማቋቋም የሚል የጋራ አላማ ያለው የኢትዮጵያ ህዝቦች ኃይሎች የህልውና ጥምረት ማቋቋማቸውን አስታውቀዋል።
ይህ ኩነት በሰሜን ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የነበረውን የበረታ የጸጥታ ስጋት ያባባሰው ሲሆን፣ የወታደራዊና የጸጥታ ስምሪቶች መጨመራቸውንና በትግራይ ክልል ውስጥ ግጭቶች በድጋሜ ሊባባሱ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች መፈጠራቸውን የሚጠቁሙ ዘገባዎች ወጥተዋል።
በዚህ ዓመት በክልሉ የአየር አገልግሎት ሲቋረጥ የመጀመሪያው አይደለም። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀደም ሲል በፌዴራል ኃይሎች፣ በአማራ ኃይሎች እና በትግራይ ኃይሎች መካከል በተፈጠሩ አዳዲስ ውጥረቶችና ግጭቶች ምክንያት ሕዳር ወር 2018 ዓ.ም መቀሌ፣ አክሱምና ሽሬ ጨምሮ ወደ ትግራይ አየር ማረፊያዎች የሚያደርጋቸውን በረራዎች አቋርጦ ነበር።
አዲስ ስታንዳርድ በሕዳር ወር 2018 ዓ.ም እንደዘገበው ለሕዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም የታቀዱ እና ወደ ትግራይ አየር ማረፊያዎች (መቀሌ፣ አክሱም፣ ሽሬ እና ሁመራን ጨምሮ) የሚደረጉ ሁሉም በረራዎች ተሰርዘው ነበር።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ካለው “ወቅታዊ ሁኔታ” ውጪ ለዛሬው የበረራ መቋረጥ ምክንያት የሆነን ሌላ የጸጥታ ክስተት አልጠቀሰም። የበረራ መቋረጡ እስከ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እስካሁን ይፋ አልተደረገም።
በዚህ ጉዳይ ላይ ትንታኔ እንዲሰጡበት የኢትዮ ፎከስ ዝግጅት ክፍል ያነጋገራቸው አቶ ደጀኔ ወርቁ የተባሉ የዓለም አቀፍ ህግና የፖለቲካል ሳይን ባለሙያ እንደገለጹት የአየር መንገዱ የትግራይ በራራ መቀጠል ይህ ክስተት የፌደራል መንግስቱ በትግራይ የአየር ክልል እና አየር ማረፊያዎች ላይ ያለውን ሙሉ ቁጥጥር እና የበላይነት በድጋሚ ማረጋገጡን ያሳያል።
አቶ ደጀኔ አክለውም ባለፈው ጊዜ ህወሓት የፌደራል መንግስቱን ስልጣንና ሉዓላዊነት ተቀብሎ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱ፣ በብዙ ተንታኞች ዘንድ የፌደራል መንግስቱ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ግቡን ማሳካቱን እንደማሳያ ይወሰዳል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ ክልል አቋርጦት የነበረውን በረራ መጀመሩ በቀጥታ የህወሓትን በጦርነት መሸነፍ ብቻ የሚያረጋግጥ ሳይሆን፣ በፌደራል መንግስቱ እና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት የሚያሳይ ክስተት ነው ሲሉ አቶ ደጀኔ አስታውቀዋል፡፡
በአጠቃላይ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ መጀመር የጦርነቱን ማክተም፣ የሰላም ስምምነቱን መተግበር እና በክልሉ የፌደራል መንግስቱ ህጋዊ ስልጣን መመለሱን የሚያሳይ እንጂ በአንድ ወገን ፍጹም ወታደራዊ መደምሰስ የተገኘ ውጤት አይደለም ሲሉ ገልጸውታል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች
ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…
የኤርትራ ወታደሮች አፋር ክልል ገብተው ውጊያ ከፈቱ
የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በመግባት ከህወሓት ታጣቂዎች ጎን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው ሲል የአፋር ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡ የአፋር ክልል…













