የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም የኤርትራው ፕሬዝዳንት “የኦሮሙማ መንግስት በሌለበት” የኦሮሙማ መንግስትን እንዋጋለን በማለት ህዝቡ ላይ የህልውና አደጋ የሚደቅን አዋጅ አውጀዋል” በሚል አመክንዮ ኦነግ መልስ ለመስጠት መግለጫ ማውጣቱ ተገልጿል፡፡
“ከፕሬዝዳንት አሳይያስ ንግግር ወዲህ ጦርነቱ በህዝባችን ላይ ያነጣጠረ መሆኑን አስተውለናል” ያሉት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ የኦሮሞ ህዝብ ሁለንተናዊ ማንነት ላይ የሚታወጅ ጦርነትን እንነቅፋለን ብለዋል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሰሜን ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስታት እና ህወሓት መካከል በአዲስ መልክ ዳግም የተቀጣጠለው ጦርነት አሁን ኤርትራንም ስቦ ወደ ደንበር ጦርነት አድጓል ያለው መግለጫው፤ ጦርነቱ ምናልባትም በሁለቱም ወገኖች በኩል ተስፋፍቶ ሌሎች አገራትንም በመሳብ በአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ እና የንብረት ውድመት ሊያስከትል ይችላል ሲል አስጠንቅቋል፡፡
የኢትዮጵያን ሥርዓተ መንግስትና የሀገርነት ህልውና ጥያቄ ውስጥ ሲከት የኖረው በዳውድ ኢብሳ የሚመራውና የመገንጠል አጀንዳ የሚያቀነቅነው ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ቀይ ባህር ለኢትዮጵያ ይገባል ሲል ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ “ቀይ ባህር ለኢትዮጵያ ህዝብ የተገባ ነው” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ትናንት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)፤ “ኤርትራ እና ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የደርግ ወታደራዊ መንግስት ውድቀትን ተከትሎ በነበራቸው ስልታዊ የፖለቲካ ትስስር ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በኢትዮጵያ ላይ የባህር በር መውጫን ዘግተዋል” ሲል ተችቷል፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ ያለው ጦርነት የተለያዩ ፍላጎቶች ያላቸው አገራትን በመጋበዝ በቀጣናው አላስፈላጊ ሰብዓዊ እና የንብረት ውድመት ከማስከተሉ አስቀድሞ ዓለማቀፉ ማህበረሰብ አገራት ላይ ግፊት እንዲያደርጉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አሳስቧል፡፡
ኦነግ በመግለጫው በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ጦርነት በተለይም በኤርትራ መንግስት በኩል የኦሮሞ ህዝብን የፈረጀ በመሆኑ የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች አንድ ላይ ቆመው ሊቃወሙት የሚገባው ነው ብሏል፡፡ግንባሩ የቀይ ባህር በር ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚገባ በመሆኑ ጥረቱን እንደሚደግፍም አቋሙን አሳውቋል፡፡
“ቀይ ባህር ለዚህ አገር ህዝብ የተገባ ነው” የሚል ርዕስ ሰጥቶት ትናንት ሰኞ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ባወጣው ይፋዊ የአቋም መግለጫ ያወጣው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦንግ)፤ “ኤርትራ እና ሕዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ (ህወሓት) የደርግ ወታደራዊ መንግስት ውድቀትን ተከትሎ በነበራቸው ስልታዊ የፖለቲካ ትስስር ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በኢትዮጵያ ላይ የባህር በር መውጫን ዘግተዋል” ሲል ተችቷል፡፡ ኦነግ “ሸፍጥ” ባለው በዚያው መንገድ ከአፍሪካ ቀንድ ትልቁን ህዝብ የያዘው አገር ወደብ አልባ ሆኖ ቀርቷልም በማለት ወቅሷል፡፡
በፍጥነት እያደገ ላለው ህዝብ እና ለኢኮኖሚው ፍላጎት መጨመር ወደ ቀይ ባህር መውጣት ለኢትዮጵያ እጅጉን አስፈላጊ ነው ያለው ኦነግ በመግለጫው፤ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የወደቡ ጉዳይ የኢትጵያን ህዝብ እጣፈንታ የሚወስን እንደመሆኑ ይህንኑን ለማረጋገጥ የሚደረጉ እርምጃዎች ወሳኝ ናቸው ብሏል፡፡
ኦነግ አክሎም የባህር በር ጥያቄው ከተመለሰ የአፋርን ህዝብ በአንድ ጥላ ስር የሚሰበስብ እንደመሆኑ አስፈላጊነቱ ዘርፈብዙ ነው ሲል በመግለጫው ጠቅሷልም፡፡ በመሆኑም የቀይ ባህር በርን ለመመለስ የሚደረገው ጥረትና እርምጃ የኢትዮጵያን ህዝብ በቀጥታ የሚመለከት ጉዳይ ነው ብሎ ኦነግ እንደሚያምንም ተጠቁሞ ጥረቱን በቀናነት እንደሚመለከተውም ተብራርቷል፡፡
ኦነግ በዚሁ መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚደረገው ጦርነት “የኦሮሞ ህዝብ ሀብት መቀራመት ላይ አይኑን የሚጥል ነው” በማለትም በጦርነቱ የኦሮሞ እና የደቡብ ኢትዮጵያን ህዝብ እጣፈንታ ለመወሰን የሚደረግ ያለውን “ውጥን” ነቅፏል፡፡
በታሪክም የዚህን አገር እጣፈንታ የወሰኑ በርካታ ጦርነቶች በሰሜን የአገሪቱ አከባቢዎች የተደረጉ ናቸው ሲል ታሪክ ያጣቀሰው የኦነግ መግለጫ፤ “ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሰሜን ኢትዮጵያ የተዋቀረው የጦር ግንባርና ወታደራዊ አቅሞች ኦሮሞ እና ኦሮሞነትን ለማጥፋት ያለመ ነው” በማለት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በጎርጎሳውያን ግንቦር 24 ቀን 2025 አደረጉ ያለውን ንግግር በዋቢነት ጠቅሷል፡፡
በፍጥነት እያደገ ላለው ህዝብ እና ለኢኮኖሚው ፍላጎት መጨመር ወደ ቀይ ባህር መውጣት ለኢትዮጵያ እጅጉን አስፈላጊ ነው ያለው ኦነግ በመግለጫው፤ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የወደቡ ጉዳይ የኢትጵያን ህዝብ እጣፈንታ የሚወስን እንደመሆኑ ይህንኑን ለማረጋገጥ የሚደረጉ እርምጃዎች ወሳኝ ናቸው ብሏልም፡፡
ኦነግ አክሎም የባህር በር ጥያቄው ከተመለሰ የአፋርን ህዝብ በአንድ ጥላ ስር የሚሰበስብ እንደመሆኑ አስፈላጊነቱ ዘርፈብዙ ነው ሲል በመግለጫው ጠቅሷልም፡፡ በመሆኑም የቀይ ባህር በርን ለመመለስ የሚደረገው ጥረትና እርምጃ የኢትዮጵያን ህዝብ በቀጥታ የሚመለከት ጉዳይ ነው ብሎ ኦነግ እንደሚያምንም ተጠቁሞ ጥረቱን በቀናነት እንደሚመለከተውም ተብራርቷል፡፡
ኦነግ በዚሁ መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚደረገው ጦርነት “የኦሮሞ ህዝብ ሀብት መቀራመት ላይ አይኑን የሚጥል ነው” በማለትም በጦርነቱ የኦሮሞ እና የደቡብ ኢትዮጵያን ህዝብ እጣፈንታ ለመወሰን የሚደረግ ያለውን “ውጥን” ነቅፏል፡፡
በታሪክም የዚህን አገር እጣፈንታ የወሰኑ በርካታ ጦርነቶች በሰሜን የአገሪቱ አከባቢዎች የተደረጉ ናቸው ሲል ታሪክ ያጣቀሰው የኦነግ መግለጫ፤ “ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሰሜን ኢትዮጵያ የተዋቀረው የጦር ግንባርና ወታደራዊ አቅሞች ኦሮሞ እና ኦሮሞነትን ለማጥፋት ያለመ ነው” በማለት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በጎርጎሳውያን ግንቦር 24 ቀን 2025 አደረጉ ያለውን ንግግር በዋቢነት ጠቅሷል፡፡

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች
ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…
የኤርትራ ወታደሮች አፋር ክልል ገብተው ውጊያ ከፈቱ
የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በመግባት ከህወሓት ታጣቂዎች ጎን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው ሲል የአፋር ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡ የአፋር ክልል…