Image

ሳዑዲ_አረቢያ በቀይ ባሕር አዲስ የባሕር ኃይል ጥምረት መቋቋሙን ገለፀች፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኦማን ከጥምረቱ ውጪ ሆነዋል፡፡

​የየመን ሁቲዎች የሚያካሂዱትን ጥቃት ተከተሎ፣ ሳዑዲ አረቢያ በቀይ ባሕር፣ በባብ ኤል-ማንደብ መደብ እና በኤደን በህረ-ሰላጤ በኩል የሚያልፉ የንግድና የኃይል ማጓጓዣ መስመሮችን ለመጠበቅ ያለመ የባሕር ኃይል መከላከያ ጥምረት ማቋቋሟን አስታወቀች።

​የሳዑዲ አረቢያ መከላከያ ሚኒስቴር ይህንን ውሳኔ ይፋ ያደረገው ከ43 ሀገራት የተወጣጡ የመከላከያ ተወካዮች እና የአውሮፓ ሕብረት ልዑካን በታደሙበት ስብሰባ ላይ ነው። ሪያድ አዲሱን ጥምረት የምትመራ ሲሆን ዋና መስሪያ ቤቱም በዚያው እንደሚሆን ተገልጿል። ይህ ጥረት የባሕር ደኅንነትን ለማጠናከር፣ የነጻ የባሕር ላይ ጉዞን ለማረጋገጥ እና ዓለም አቀፍ የንግድና የኃይል አቅርቦቶችን ለመጠበቅ ያለመ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

​ይህን ማዕቀፍ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኩዌት፣ ባህሬን፣ ካታር፣ ፓኪስታን፣ ቱርክ፣ ግብፅ፣ ዮርዳኖስ፣ የመን፣ ባንግላዴሽ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ እና ሶማሊያ ጨምሮ 14 ሀገራት በይፋ ደግፈውታል። ጥምረቱ የጋራ እቅድ፣ ልምምዶችን፣ የመረጃ ልውውጥን እና የተቀናጁ የባሕር ላይ እንቅስቃሴዎችን የሚያካትት መከላከያ ነክ ስምምነት ሲሆን፣ በየትኛውም እንቅስቃሴ ላይ መሳተፍ የየሀገራቱ የሉአላዊነት ውሳኔ ሆኖ ይቀጥላል።

​ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ ትብብር ምክር ቤት (GCC) ስድስት አባል ሀገራት መካከል ሁለቱ ማለትም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኦማን አለመካተታቸው ትኩረት ስቧል። የሁለቱ ሀገራት ከጥምረቱ ውጪ መሆን በቀጠናው ባላቸው ስትራቴጂካዊ ቦታ እና የባሕር ደኅንነት ፍላጎቶች አንጻር ከፍተኛ ትርጉም ያለው መሆኑን ሮይተርስ አመልክቷል።

​ይህ ጅማሮ ሁቲዎች በሳዑዲ አረቢያ ላይ የባሕር ላይ እገዳ መጣላቸውን ካወጁ እና በቀይ ባሕር በሚንቀሳቀሱ የሳዑዲ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ የመጣ ነው። ሳዑዲ አረቢያ በበኩሏ በየመን በሚገኙ የሁቲ ወታደራዊ ተቋማት ላይ የአየር ጥቃቶችን ስታካሂድ ቆይታለች።

​ይህ አዲስ ስብስብ የአውሮፓ ሕብረት የሚያካሂደውን «ኦፕሬሽን አስፒደስ» ጨምሮ ከነባር የምዕራባውያን የባሕር ደኅንነት ስራዎች ጎን ለጎን የሚሰራ ቢሆንም፣ የጥምረቱ ዝርዝር ተልዕኮ፣ የተቋማዊ መዋቅር እና ከነባር ተልዕኮዎች ጋር የሚኖረው ግንኙነት ወደፊት የሚወሰን ይሆናል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026