የኤርትራ የሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል፣ ደካማ ኢኮኖሚ፣ ወታደራዊ ውስንነቶች፣ ተቋማዊ የመተካካት ሥርዓት አለመኖር እና በአንድ መሪ ላይ ብቻ ጥገኛ መሆን ተዳምረው ሀገሪቱን አለከፋ የሀገርነት ቀውስ እንደዳረጓት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ አስረድተዋል።
ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመከላከያ ኮሌጅ ዓመታዊ የብሔራዊ ደህንነት ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ጌታቸው፤ የኢትዮጵያን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ኤርትራ ውስጥ ካለው የሕዝብ ቁጥር መቀነስ እና ከተቋማዊ መዳከም ጋር በማነጻጸር፣ የሁለቱ አገራት ተለዋዋጭ የሕዝብ ቁጥር እውነታዎች የቀጠናውን የወደፊት የደኅንነት ሁናቴ ለመረዳት ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን አብራርተዋል። አቶ ጌታቸው ይህንን የሕዝብ ቁጥር መከራከሪያ ይበልጥ በማስፋት፣ ነገር ግን ከተለየ እይታ አንጻር አቅርበውታል።
የባሕር በር ለማግኘት ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የሚቀርበው የሕዝብ ቁጥር ዕድገት መከራከሪያ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ በመሄድ ወደ ሰፊ ብሔራዊ የደኅንነት ትርክት እየተቀየረ ይገኛል። በጥቅምት ወር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎች በፍጥነት እያደገ ካለው የሕዝብ ቁጥር አንጻር ፍትሐዊ ጥያቄ መሆኑን ገልጸዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ 118ኛውን የመከላከያ ሠራዊት ቀን በዓል በተከበረበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ “የሕዝባችን ቁጥር አሁን 130 ሚሊዮን ደርሷል። በሚቀጥሉት 25 ዓመታት ውስጥ ደግሞ 200 ሚሊዮን ይደርሳል” ያሉ ሲሆን አክለውም፤ “እንዴት በ2 ሚሊዮን ማህበረሰብ ጥቅም የ200 ሚሊዮን ሕዝብ ጥቅም ይዘጋል? ይህ ፍትሐዊ አይደለም፣ ዓለም አቀፍ ሕግም አይደለም፣ ምክንያታዊም አይደለም” ማለታቸው ይታወሳል።
“በዘልማድ ኤርትራ ሶስት ሚሊዮን ህዝብ አላት ይባላል። በጣም የሚታመኑ ምንጮች የሚገልፁት 1.9 ሚሊዮን በላይ ህዝብ እንደሌላት ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው፤ “በአውሮፓ ካሉት አጠቃላይ የአፍሪካ ስደተኞች መካከል 30 በመቶ ያህሉ ኤርትራውያን ናቸው” ብለዋል።
አክለውም፤ “በአሁኑ ሰዓት ከከረን ይልቅ ካምፓላ ውስጥ ብዙ ኤርትራዊ አለ። ከረን የኤርትራ ሁለተኛ ከተማ ነው” ያሉት አማካሪው፤ “ስለዚህ የኤርትራ ሀገርነትም ራሱ ፈተና ውስጥ የወደቀ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ይሄ ዴሞግራፊክ ቀውስ የህልውና ቀውስ ነው። አሁን ኤርትራ ውስጥ የቀሩት አረጋውያን ብቻ ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል።
እንደ አቶ ጌታቸው ገለፃ፤ «የሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል» የኤርትራ ሀገርነት እየገጠመው ያለው ብቸኛ ፈተና አይደለም። አገር ሆና የተመሠረተችበት መንገድ በኤርትራ ሀገርነት ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን እና ጥልቅ መዋቅራዊ ቀውስን እንደሚያንጸባርቅ አመልክተዋል።
ይህ «ብዙ ትንታኔ የሚያስፈልገው አይደለም» ካሉ በኋላ፣ የኤርትራ ሀገረ መንግስት ምስረታ ሂደት ራሱ ኢትዮጵያን በማፍረስ ኢትዮጵያን በማዳከም ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
አማካሪው አክለውም “ኤርትራን ወደ ነፃነት እንቅስቃሴ ያስገቡት ሀይሎች የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉ ሀይሎች ናቸው” ያሉ ሲሆን፣ የኤርትራ የሀገርነት መቀጠልን አለመቀጠል ስሌት ሁሌም ኢትዮጵያን ከማዳከም ጋር የተያያዘ ነው” ብለዋል። ንግግራቸው፤ አቶ ጌታቸው የኢትዮጵያ መንግስታት መምጣትም ሆነ መሄድ መውደቅም ሆነ መነሳት ቀጥታ ከኤርትራ ጥያቄ አመለላሳችን ጋር የተያያዘ ነጥብ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
“የተከታታይ የኢትዮጵያ መንግሥታት መነሳትና መውደቅ፣ መምጣትና መሄድ፣ የኤርትራን ጥያቄ እንዴት እንደያዝነው ከሚለው ጉዳይ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነበር» ያሉት ጌታቸው፣ ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከምታደርገው የወደብ ፍለጋ፣ የቀጠናዊ ትስስር እና የብሔራዊ ደኅንነት ጥረት ጋር የማይነጣጠል መሆኑን አስገንዝበዋል።
ይህንን ታሪካዊ መከራከሪያ ለማብራራት፤ አቶ ጌታቸው በዘውድ ሥርዓቱ ወቅት የነበረውን የኢትዮ-ኤርትራ ፌዴሬሽን መፍረስ ተከትሎ የተነሱ ክርክሮችን ጠቅሰዋል። በወቅቱ የፌዴሬሽኑን መፍረስ ተቃውመው የነበሩትንና በምትኩ ኢትዮጵያ የዜጎቿን ኑሮ ማሻሻል ላይ ቅድሚያ መስጠት አለባት ብለው ተከራክረው የነበሩትን ከፍተኛ ባለሥልጣን ፀሀፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስን ንግግር ጠቅሰዋል።
«ዋናው ሥራችን ሕዝባችንን መመገብ፣ ረሃባቸውን ማስታገስ እና የተቸገረውን ሕዝባችንን ማልበስ መሆን አለበት» ሲሉ ጸሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ መናገራቸውን ያስታወሱት ጌታቸው፤ ብልጽግናን ማምጣት በግዴታ ሳይሆን በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ አንድነት እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ያመቻች ነበር ሲሉ ተከራክረዋል።
«ኤርትራ እንደ አገር ስትመሠረት ‘በሮማንቲክ እሳቤ’ ላይ ተመስርታ ነበር» ያሉት ጌታቸው፤ ኤርትራ «ሰው ሠራሽ አካል» (artificial entity) መሆኗንና የአገሪቱ አመራር ቀጣይነት ላለው ሀገርነት የሚያስፈልጉትን ተቋማዊ መሠረቶች ወደ ጎን በመተው፣ በነፃነት ትግሉ ዙሪያ ታሪካዊ ማንነትን ለመገንባት መሞከሩን ገልጸዋል።
እንደ እሳቸው አገላለጽ ከሆነ፤ ይህ አካሄድ በትጥቅ ትግሉ ወቅት በዳበረው እና ደጋግመው «የሳህል ዲሲፕሊን» ሲሉ በገለጹት መርህ ላይ ብቻ ጥገኛ የሆነ የአስተዳደር ዘይቤን ፈጥሯል።
“የኤርትራ በአገርነት ፈተናው ውስጥ አሁን ያለው ኢሳይያስ በሳህል ዲሲፕሊን ብቻ ነው ያን አገር መምራት የሚችለው” ያሉት ጌታቸው፣ ማንኛውም ዘመናዊ መንግሥት በጦርነት ጊዜ የአስተዳደር ስልቶች ብቻ እስከ ወዲያኛው ሊቀጥል እንደማይችል ተናግረዋል።
ይህ ግምገማ ኤርትራ የዓሰብን ወደብ ለኢትዮጵያ የንግድ አገልግሎት በድጋሚ ለመክፈት አሁንም ፈቃደኛ ያልሆነችበትን ምክንያት አመላክቷል።
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በቅርቡ የሰጡትን አስተያየት ያነሱት አማካሪው፤ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ ጅቡቲ ለኢትዮጵያ ንግድ የምትሰጠው አገልግሎት «ተፈጥሮ የሰጠቻትን ፀጋ » መሆኑን እና ኤርትራም ከጅቡቲ ጋር ለመወዳደር ብቻ ብላ ዓሰብን እንደማትከፍት መናገራቸውን አስታውሰዋል። ሆኖም ይህ ስሌት ከውጭ ይልቅ በኤርትራ የሀገር ውስጥ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ መሆኑን ጌታቸው አክለው ተከራክረዋል።
“የዓሰብን ወደብ መጠቀም በጀመርንበት ዕለት፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞችና የትራፊክ ፍሰት በዚያ ቀጠና ውስጥ ይጥለቀለቃሉ” ያሉት ጌታቸው፤ የንግድ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች እንደገና ከጀመሩ፤ “የኤርትራ ወጣት መኖሪያው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የሚሆነው» ብለዋል። ይህም የኤርትራ መንግሥት ያለገደብ የሚያካሂደውን የግዳጅ ውትድርና እና ማዕከላዊ የፖለቲካ ቁጥጥርን ጠብቆ ለማቆየት ከቀን ወደ ቀን አስቸጋሪ እንደሚያደርገው አመልክተዋል።
ጌታቸው ይህንን መከራከሪያውን ወደ ኤርትራ ሰፊ ወታደራዊ አቋም በማሻገር፣ «የሕዝብ ቁጥር መመናመኑ» የአገሪቱን መደበኛ ወታደራዊ አቅም ጭምር እንዳዳከመው ገልጸዋ። ከግብፅ ቀጠናዊ የደኅንነት ስትራቴጂ ጋር በማነጻጸር፤ ኤርትራ ከመደበኛ ወታደራዊ ኃይል ይልቅ ይበልጥ ቀጥተኛ ባልሆኑና አነስተኛ ወጪ በሚጠይቁ ዘዴዎች ላይ ጥገኝነቷን እያሳደገች መሆኑን ገልጸዋል።
“የኤርትራ ሰራዊት ከግብፅ ትልቅ ትምህርት የተማረው ምንድነው?” ሲሉ የጠየቁት አማካሪው፤ ዋና የፖለቲካ አጀንዳቸውን የማስፈፀም ትልቅ ብቃት አዳብረዋል።” ብለዋል።
[6/27/2026 11:23 AM] t V: እንደ እሳቸው ገለጻ፤ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግን መደበኛ ወታደራዊ ፍልሚያ ለመቋቋም የሚያስችል የሕዝብ ቁጥርም ሆነ የቴክኖሎጂ አቅም የላትም።
«የውጊያ ኃይልህን መልሰህ የመተካት አቅም ሳይኖርህ እንዲሁም ምንም ዓይነት የቴክኖሎጂም ሆነ የሕዝብ ቁጥር ብልጫ ሳይኖርህ በአሮጌዎቹ ቲ-54 እና ቲ-55 ታንኮች ላይ ብቻ ተመስርተህ፤ መደበኛውን ግጭት ከጥቂት ቀናት በላይ ልትቋቋም አትችልም» ሲሉ ጌታቸው ተናግረዋል። ኤርትራ ያላት «ስትራቴጂካዊ ጥልቀት» ውስን መሆኑንም የጠቀሱት አማካሪው፤ ኤርትራ፣ በአንድ አቅጣጫ ከተሰበረ የኢትዮፕያ ኃይል ወደ መሃል ለመግባት ቀናት ብቻ ነው የሚፈልገው ብለዋል።
እነዚህ ወታደራዊ ውስንነቶች አስመራ በቀጥተኛ ግጭት ፋንታ በወኪል ግጭቶች ላይ እንድታተኩር አድርገዋታል። «በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ኢሳይያስ የኢትዮጵያን አለመረጋጋት ለራሳቸው ቀጣይነት ያለው ህልውና ብቸኛው ዋስትና አድርገው ይመለከቱታል» ሲሉ ተናግረዋል።
አስመራ የኤርትራን ኃይሎች በቀጥታ ከመሰማራት ይልቅ፣ መጠነ-ሰፊ መደበኛ ውጊያዎችን በማስወገድ ስትራቴጂካዊ ግቦችን ለማሳካት አማካሪዎችን፣ አሰልጣኞችን እና ወኪል ተዋናዮችን መላክን ጨምሮ በቀጠናው በሌሎች አካባቢዎች ከሚታዩት ጋር ተመሳሳይ በሆኑ ቀጥተኛ ያልሆኑ ዘዴዎች ላይ ጥገኝነቷን እያሳደገች መሆኑን አብራርተዋል። ለዚህም ሱዳንን እንደ ምሳሌ የጠቀሱት ጌታቸው፤ ኤርትራ ትላልቅ የጦር ክፍሎችን ከማሰማራት ይልቅ ወታደራዊ ባለሙያዎችን በስውር ማስረጽን እንደምትመርጥ ገልጸዋል።
ጌታቸው እንዳሉት፤ «አጀንዳቸውን በአነስተኛ ወጪ ለመፈጸም፣ ኢሳይያስ በከፍተኛ ሁኔታ ‘ዩዝፉል ኢዲየትስ’ (useful idiots) ላይ ይተማመናሉ» ያሉት ጌታቸው፤ በአስማራ ከነበረ አንድ ጣሊያናዊ ዲፕሎማት ጋር የተደረገ ነው ያሉትን ውይይት አስታውሰዋል።
ኤርትራ የተለያዩ የኢትዮጵያን የትጥቅ ንቅናቄዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከፌዴራል ኃይሎች ጋር እንዲጋጩ በማበረታታት፣ ግጭቱን ከራሷ ድንበር ለማራቅ እንደምትፈልግ ተከራክረዋል። ይህ ስትራቴጂ አስመራ በቀጥታ ወታደራዊ ፍልሚያ ለመሳተፍ አቅም እንደሌላት የሚያንጸባርቅ ሲሆን፣ በምትኩ በረጅም ጊዜ የሀገር ውስጥ አለመረጋጋት ኢትዮጵያን ለማዳከም እንደምትጥር ያሳያል ብለዋል።
በተጨማሪም እ.ኤ.አ. በህዳር 2022 የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ የኤርትራ ስትራቴጂካዊ ስሌቶች መቀየራቸውን ገልጸዋል።
እንደ ጌታቸው አገላለጽ፤ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ ስምምነቱን እንደ ሽንፈት የሚመለከተው የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን (ሕወኃት) የማጥፋት ፍላጎታቸውን ማሳካት ባለመቻሉ ነው ብለዋል።
«ኢሳይያስ አላማውንን የሚያስፈጽሙባቸው አነስተኛ ወጪ የሚጠይቁ ተኪ ኃይሎች መቼም ቢሆን አያጡም» ያሉት ጌታቸው፤ ኤርትራ ፋኖን፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ጨምሮ ለተለያዩ የታጠቁ ቡድኖች የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀያይር ገልጸዋል። አክለውም «ዛሬ ላይ… ኢሳይያስ እና ሕወኃት ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ በይፋ በታወጀ አጀንዳ ሥር የተባበሩ የፖለቲካ አጋሮች ሆነዋል» ብለዋል።
እነዚህን ትችቶች ቢሰነዘሩም፣ ጌታቸው በኤርትራ መንግሥት እና በኤርትራ ዜጎች መካከል ልዩነት እልዳለ ገልጸዋል።
«እኔ አጽንኦት የምሰጠው በኤርትራ መንግሥት ላይ ነው» ያሉት አማካሪው፤ የኤርትራ ህዝብ ወዳጃችን ነው ተብሎ ሊሰራበት ይችላል። በሁሉም አካባቢዎች ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ጥቅሟ መከበሩ ጥቅማችን ነው የሚሉ ሀይሎች መበራከት መቻል አለባቸው ብለዋል።
ኢኮኖሚካሊ የራሳችን ስራ ላይ በደንብ ማተኮር መቻል አለብን ብቻ ሳይሆን አጓጊ ማድረግ መቻል አለብን ኢትዮጵያ አጓጊ ነው ማድረግ ያለብን ሲሉ ገልጸው፤ ሚሊተሪ አልመክራችሁም ሁሉም አቅማችን፣ ዘመናዊ ትጥቁ ሁሉም ተጠናክሮ ዲተርም ማድረግ መሆን መቻል አለበት ሲሉ አክለዋል።
ወደ ኢትዮጵያ የራሷ የደኅንነት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች የተመለሱት ጌታቸው፤ የአገሪቱ ዋና መከላከያ በውጭ ሥጋቶች ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ የሀገር ውስጥ አንድነትን ማጠናከር እንደሆነ ተከራክረዋል።
«የመጀመሪያው መከላከያችን የውስጥ ጥንካሬያችን ነው» ያሉ ሲሆን፣ «የሌላ ወገን ድክመት የእራስህን አቅም ሊተካ አይችልም» በማለት፣ ኤርትራ ኢትዮጵያን ለማስፈራራት ያላት አቅም በመጨረሻም የውስጥ አለመረጋጋትን በመጠቀም ላይ የተመሠረተ መሆኑን አስገንዝበዋል።
«በእውነቱ የኤርትራ ሥርዓት ኢትዮጵያን ለመውረር የሚያስችል ትክክለኛ ወታደራዊ አቅም ሊኖረው የሚችለው፣ የጀመረው የውስጥ አለመረጋጋት ዘመቻ የውስጥ ጥንካሬያችንን ሙሉ በሙሉ መሠረት ሲያናጋው ብቻ ነው» ብለዋል። ከዚህ ውጭ ግን ኤርትራ ቀጥተኛ ግጭትን ለመቋቋም የሚያስችል «የሕዝብ ቁጥር፣ ወታደራዊም ሆነ የቴክኖሎጂ ብልጫ» እንደሌላት በመጥቀስ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የታጠቁ ቡድኖችን ማደራጀት ለአገሪቱ የተጋረጠው ዋናው የደኅንነት ሥጋት መሆኑን አቶ ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል።
አቶ ጌታቸው ምንም እንኳን የንግግራቸው አብዛኛው ክፍል በኤርትራ ላይ ያተኮረ ቢሆንም፣ ደጋግመው ኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት ሲጠቅሱ ተደምጠዋል። ቀደም ሲል በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተነሱትን ጭብጦች በማስተጋባት፣ የኢትዮጵያ እያደገ የመጣው የሕዝብ ቁጥር አስተማማኝ የባሕር በር አገልግሎት እንደሚያስፈልገው ጠቅሰው፣ ነገር ግን በታሪካዊ መከራከሪያዎች ላይ ብቻ መተማመንን አስጠንቅቀዋል።
«በዲፕሎማሲው ረገድ እጅግ በርካታ ሰዎች መከራከሪያቸውን በታሪክ ላይ ብቻ ይገድባሉ» ያሉት ጌታቸው፣ «የ130 ሚሊዮን ሕዝብ ቁጥር ያለው አገር የባሕር በር አጥቶና ታፍኖ ሊቀጥል አይችልም። ለአላማችን ከባለፈው ታሪክ ይልቅ የአሁኑ እና የወደፊቱ ጊዜ እጅግ የላቀና ጠንካራ መከራከሪያ ይሆኑናል» ብለዋል።
አማካሪው አክለውም «ዋናው መከራከሪያችን ትኩረት ማድረግ ያለበት በዘመናዊው የወደብ አገልግሎት የማግኘት መብታችን ላይ መሆን አለበት። ‘ወደቡ ቀድሞ የእኛ ነበረ’ በሚል ያለፈ ውርስ ክርክር መሆን የለበትም» ሲሉ አስገንዝበዋል።
ጌታቸው ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ፤ የኤርትራ የሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል፣ ደካማ ኢኮኖሚ፣ ወታደራዊ ውስንነቶች፣ ተቋማዊ የመተካካት ሥርዓት አለመኖር እና በአንድ መሪ ላይ ብቻ ጥገኛ መሆን ተዳምረው ሀገሪቱን አለከፋ የሀገርነት ቀውስ እንደዳረጓት አስረግተዋል።
«የእኔ የጸና እምነት ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ ከዚህ ዓለም ሲለዩ፣ ኤርትራ እንደ አንድ የተረጋጋና የተቀናጀ አገር ልትቀጥል አትችልም፤ አትቀጥልምም» ያሉት ጌታቸው፤ ኢትዮጵያ የማይቀሬ ነው ካሉት ከዚህ የሽግግር ወቅት ጋር በተያያዘ በዲፕሎማሲው፣ በኢኮኖሚውና በፖለቲካው ረገድ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርግ አሳስበዋል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች
ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…













