ህወሓት የአውሮፓ ህብረት በትግራይ “ትይዩ ምክር ቤት አቋቁሟል” ማለቱ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው በማለት መግለጫውን አስተባበለ፡፡ የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያወጣውን መግለጫ በመቃወም ይፋዊ ምላሽ የሰጠ ሲሆን የግዳጅ ምልመላም ሆነ ትይዩ ምክር ቤት በትግራይ የለም ሲል አስታወቀ።
ህወሓት አክሎም የህብረቱ መግለጫ መሬት ላይ ያለውን እውነታ የማያንጸባርቅና በተሳሳተ መረጃ ላይ የተመሰረተ ነው በማለት ወቅሷል።
ህወሓት በትግራይ ክልል “ትይዩ ክልላዊ ምክር ቤት” አቋቁሟል ተብሎ የቀረበበትን ክስ “ፈጽሞ መሰረተ ቢስ” ነው ሲል ውድቅ አድርጎታል። ህወሓት አክሎም በትግራይ ህዝብን የሚወክል ሌላ ምክር ቤት ኖሮ እንደማያውቅና በቅርቡ ስራ የጀመረው ቀደም ሲል በምርጫ የተመረጠው ብቸኛው ህጋዊ የትግራይ ክልል ምክር ቤት መሆኑን አስታውቋል።
በተመሳሳይ መልኩ ድርጅቱ “የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ” እያካሄደ ነው የተባለውን ውንጀላም ምንም ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ የሌለው ነው በማለት ያስተባበለ ሲሆን ዓለም አቀፍም ተቋማት እና በሀገር ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህንን በተመሳሳይ እንደ ህብረቱ መቃወማቸው ይታወቃል።
የፌደራል መንግስቱ የዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነቱን በተከታታይ እያናጋ መሆኑን የገለጸው ህወሓት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሳይቀሩ የውሉን መሰረት እየካዱና አንዱን ፈራሚ አካል ህወሓትን ህገ-ወጥ ለማድረግ እየሰሩ ነው በማለት ከስሷል። በዚህም ምክንያት የሰላም ስምምነቱ ዋና ዋና ድንጋጌዎች ሳይተገበሩ መቅረታቸውንና የትግራይ ህዝብ አሁንም በነዳጅና የንግድ ዕቃዎች እገዳ ሳቢያ ለከፋ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግር መጋለጡን ድርጀቱ ጠቅሷል።
የጸጥታ ሁኔታውን በተመለከተም፣ በትግራይ ዙሪያ ከፍተኛ የወታደራዊ ዝግጅት፣ የድሮን ጥቃቶችና የአየር ላይ ክትትሎች እየተደረጉ በመሆኑ የጦርነት ስጋቱ እየጨመረ ነው ሲል የገለጸው ድርጅቱ የክልሉ ባለስልጣናት ህዝባቸውን ከህልውና አደጋ የመጠበቅ ህጋዊና ሞራላዊ ግዴታ እንዳለባቸው ለህብረቱ ምላሽ ሰጥቷል።
ህወሓት አክሎም እነዚህ ሁሉ ጥሰቶች እየተፈጸሙ ባሉበት ወቅት የአውሮፓ ህብረት የልዑካን ቡድን በፌደራል መንግስቱ ላይ ግልጽ ትችት ከመሰንዘር መቆጠቡና ዝምታን መምረጡ እንዳሳሰበው አስታውቋል።
ድርጅቱ ለህብረቱ በፃፈው ይፋዊ ተቃውሞ ላይ አሁንም ቢሆን ውይይትና የፖለቲካ ንግግር ብቸኛውና ስትራቴጂካዊ አማራጩ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጣለሁ ያለ ሲሆን፤ የአውሮፓ ህብረትና ሌሎች አለም ዓቀፍ አጋሮች የፌደራል መንግስቱ ያለምንም መዘግየት ወደ እውነተኛ ውይይት እንዲመጣ ተጽዕኖ ማድረግ አለባቸው ብሏል።ህወሓት የአውሮፓ ህብረት በትግራይ “ትይዩ ምክር ቤት አቋቁሟል” ማለቱ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው በማለት መግለጫውን አስተባበለ፡፡ የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያወጣውን መግለጫ በመቃወም ይፋዊ ምላሽ የሰጠ ሲሆን የግዳጅ ምልመላም ሆነ ትይዩ ምክር ቤት በትግራይ የለም ሲል አስታወቀ።
ህወሓት አክሎም የህብረቱ መግለጫ መሬት ላይ ያለውን እውነታ የማያንጸባርቅና በተሳሳተ መረጃ ላይ የተመሰረተ ነው በማለት ወቅሷል።
ህወሓት በትግራይ ክልል “ትይዩ ክልላዊ ምክር ቤት” አቋቁሟል ተብሎ የቀረበበትን ክስ “ፈጽሞ መሰረተ ቢስ” ነው ሲል ውድቅ አድርጎታል። ህወሓት አክሎም በትግራይ ህዝብን የሚወክል ሌላ ምክር ቤት ኖሮ እንደማያውቅና በቅርቡ ስራ የጀመረው ቀደም ሲል በምርጫ የተመረጠው ብቸኛው ህጋዊ የትግራይ ክልል ምክር ቤት መሆኑን አስታውቋል።
በተመሳሳይ መልኩ ድርጅቱ “የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ” እያካሄደ ነው የተባለውን ውንጀላም ምንም ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ የሌለው ነው በማለት ያስተባበለ ሲሆን ዓለም አቀፍም ተቋማት እና በሀገር ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህንን በተመሳሳይ እንደ ህብረቱ መቃወማቸው ይታወቃል።
የፌደራል መንግስቱ የዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነቱን በተከታታይ እያናጋ መሆኑን የገለጸው ህወሓት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሳይቀሩ የውሉን መሰረት እየካዱና አንዱን ፈራሚ አካል ህወሓትን ህገ-ወጥ ለማድረግ እየሰሩ ነው በማለት ከስሷል። በዚህም ምክንያት የሰላም ስምምነቱ ዋና ዋና ድንጋጌዎች ሳይተገበሩ መቅረታቸውንና የትግራይ ህዝብ አሁንም በነዳጅና የንግድ ዕቃዎች እገዳ ሳቢያ ለከፋ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግር መጋለጡን ድርጀቱ ጠቅሷል።
የጸጥታ ሁኔታውን በተመለከተም፣ በትግራይ ዙሪያ ከፍተኛ የወታደራዊ ዝግጅት፣ የድሮን ጥቃቶችና የአየር ላይ ክትትሎች እየተደረጉ በመሆኑ የጦርነት ስጋቱ እየጨመረ ነው ሲል የገለጸው ድርጅቱ የክልሉ ባለስልጣናት ህዝባቸውን ከህልውና አደጋ የመጠበቅ ህጋዊና ሞራላዊ ግዴታ እንዳለባቸው ለህብረቱ ምላሽ ሰጥቷል።
ህወሓት አክሎም እነዚህ ሁሉ ጥሰቶች እየተፈጸሙ ባሉበት ወቅት የአውሮፓ ህብረት የልዑካን ቡድን በፌደራል መንግስቱ ላይ ግልጽ ትችት ከመሰንዘር መቆጠቡና ዝምታን መምረጡ እንዳሳሰበው አስታውቋል።
ድርጅቱ ለህብረቱ በፃፈው ይፋዊ ተቃውሞ ላይ አሁንም ቢሆን ውይይትና የፖለቲካ ንግግር ብቸኛውና ስትራቴጂካዊ አማራጩ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጣለሁ ያለ ሲሆን፤ የአውሮፓ ህብረትና ሌሎች አለም ዓቀፍ አጋሮች የፌደራል መንግስቱ ያለምንም መዘግየት ወደ እውነተኛ ውይይት እንዲመጣ ተጽዕኖ ማድረግ አለባቸው ብሏል።