Image

በትግራይ አፈሳው የፈጠረው የፍርሃት ድባብ

ሂዩማን_ራይትስ ዎች የ ትግራይ ባለሥልጣናት ሲቪሎችን በግዳጅ ለውትድርና እየመለመሉ ነው ሲል ከሰሰ፤ ምልመላው «የፍርሃት ድባብ» መፍጠሩንም ገልጿል፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሂዩማን ራይትስ ዎች፤ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ባለሥልጣናት ዕድሜያቸው 16 የሆኑ ሕፃናትን ጨምሮ በሲቪሎች ላይ ያነጣጠረ የግዳጅ ውትድርና ምልመላ ዘመቻ እያካሄዱ ነው ሲል የከሰሰ ሲሆን፣ የክልሉ ኃይሎች ቢያንስ ከሚያዝያ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀድሞ ተዋጊዎችን፣ ወንዶችንና ታዳጊዎችን እያገቱ መሆኑን ገልጿል።

ዛሬ የወጣው የድርጅቱ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ ይህ የምልመላ ዘመቻ በክልሉ ውስጥ «የፍርሃት ድባብ» የፈጠረ ሲሆን፥ ሲቪሎች ከጎዳናዎች፣ ከሥራ ቦታዎች፣ ከመኖሪያ ቤቶች እና ከባህላዊ ወርቅ ማውጫ ሥፍራዎች እየተያዙ ወደ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፖች እየተወሰዱ ነው።

በሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌቲሺያ ባደር «የትግራይ ባለሥልጣናት ወንዶችንና ታዳጊዎችን በግዳጅ ለመመልመል የሚያካሂዱት ዘመቻ በክልሉ ውስጥ የፍርሃት ድባብ እየፈጠረ ነው» ያሉ ሲሆን፤ የክልሉ ባለሥልጣናት ዘመቻውን በአስቸኳይ እንዲያቆሙና ያለፍላጎታቸው የተመለመሉትን ወደ ቤታቸው እንዲመልሱ ጥሪ አቅርበዋል።

ለሕዝቡ ሥጋት ምላሽ የሰጡት በቅርቡ እንደገና በተቋቋመው የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አብርሃም ሐጎስ፤ የክልሉ መንግስት በማስገደድ የተከናወነ ማንኛውንም የሰዎች ቅስቀሳና ምልመላ እንደሚመረምርና ጥፋተኞችንም ተጠያቂ እንደሚያደርግ ለትግራይ ቴሌቪዥን ገልጸዋል። አብርሃም ትግራይ አሁንም የህልውና አደጋ እየገጠማት መሆኑን ቢገልጹም፤ ክልሉን መከላከል በሕዝብ ግንዛቤ፣ በጋራ መግባባት እና በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

«ትግራይ የህልውና አደጋ እየገጠማት ነው፤ ሕዝቡም ራሱን የመከላከል ኃላፊነት አለበት» ያሉት ኃላፊው፤ «ሆኖም ከመንግሥት መመሪያ ውጭ እና ያለሕዝቡ እምነትና ፈቃድ የተከናወነ ማንኛውም ምልመላ ካለ በጥልቀት ይመረመራል» ብለዋል። ክልላዊ መንግሥቱ ያለፈቃድ ምልመላ ባካሄዱ ማንኛቸውም የጸጥታ አካላት ወይም የአካባቢው አስተዳደር ባለሥልጣናት ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ገልጸዋል።

የመንግሥት ምላሽ የመጣው በትግራይ ውስጥ ከፍተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ ውጥረት ባለበት እንዲሁም ባለሥልጣናት ስለሚመጡ የጸጥታ ሥጋቶች በተደጋጋሚ በሚያስጠነቅቁበት እና በክልሉ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ አለመግባባቶች ሳይፈቱ በቀጠሉበት ወቅት ነው።

ይህ አዲስ ውዝግብ የመጣው በትግራይ ደካማ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ሥጋቶች እየጨመሩ ባሉበት ወቅት ነው። የክልሉ ባለሥልጣናት በፕሪቶሪያ ስምምነት የተገኘው ሰላም አሁንም ለአደጋ ተጋላጭ መሆኑን በተደጋጋሚ ያስጠነቀቁ ሲሆን፤ ታዛቢዎችም እየጨመረ የመጣው የፖለቲካ ውጥረት በውይይት ካልተፈታ መረጋጋትን ይበልጥ ሊያናጋው እንደሚችል አሳስበዋል።

ባለፈው ግንቦት ወር 2018 ዓ.ም የመቀሌ፣ የሽሬ፣ የአክሱም፣ የአድዋ፣ የአዲግራት፣ የውቅሮ እና የሌሎች አካባቢ ነዋሪዎች ቤት ለቤት ፍተሻዎችን፣ የዘፈቀደ እስራቶችን እና ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ጣቢያዎች ማዘዋወርን ያካተቱ የተቀናጁ ዘመቻዎች መኖራቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። በርካታ ቤተሰቦች ምልመላውን ለማስቀረት ልጆቻቸውን እንደደበቁ ወይም ወደ ሌላ አካባቢ እንደላኳቸውም አክለው ተናግረዋል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026