Image

  • ትግራይ በምክክሩ እንደማትሳተፍ ህወሓት አስታውቋል

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአራት ዓመት በላይ ከወሰደ የተወካዮች መረጣ፣ አጀንዳ ማሰባሰብ እና ሌሎች ተግባራት በኋላ ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም የመጨረሻውን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አስጀምሯል።

ህወሓት ዳግም ያቋቋመውና ህጋዊ እውቅና የሌለው የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ሀገራዊ የምክክር መድረኩን ውድቅ በማድረግ በሂደቱ ላይ እንደማይሳተፍ አስታውቋል፡፡

በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሃት) ዳግም የተቋቋመው የትግራይ ክልላዊ መንግሥት እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የምክክር ሂደት ውድቅ ማድረጉን ያስታወቀ ሲሆን፥ «ተቀባይነት የሌለው» ሲል በገለጸው የውይይት መድረክ ላይ የክልሉ መንግሥትም ሆነ የትግራይ ሕዝብ አልተወከሉም ብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ ‘አዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር’ በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ ክልሎች፣ ወረዳዎች፣ ከፌደራል እንዲሁም በውጭ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተወጣጡ ከአራት ሺህ ሰዎች ይሳተፋሉ።

ዛሬ የተጀመረው ጉባኤ ከ30 እስከ 35 ቀናት ይወስዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ለአንድ ወር በአንድ ስፍራ የሚቆዩት ተሳታፊዎች ምክክር የሚያደርጉት ኮሚሽኑ በሰኔ አጋማሽ ይፋ ባደረጋቸው ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ነው። ኮሚሽኑ ይፋ ያደረጋቸው አጀንዳዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ የክርክር ነጥብ የሆኑ እንደ የሕገ መንግሥት መሻሻል፣ የመንግሥት ቅርፅ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ “ሕጋዊ አቋም” ያሉ ጉዳዮችን በውስጣቸው ይዘዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን፤ ኮሚሽናቸው ሊተገብረው ያቀደው የአገራዊ ምክክር ሥነ ዘዴ በሌሎች ከአገራት በተካሄዱ ተመሳሳይ ሂደቶች ተግባራዊ ያልተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ አገራዊ ምክክር ጉባኤው በምን ዓይነት ቅርጽ እንደሚካሄድ በዝርዝር አብራርተዋል። ዛሬ የሚካሄደው የግማሽ ቀን ሥነ ሥርዓት “የጉባኤው ማስጀመሪያው ሥነ ሥርዓት” ነው።

በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ ከሀገር ውስጥ ታዳሚዎች በተጨማሪ “የአፍሪካ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት፣ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ኤምባሲዎች፣ የውጭ አገር ሚሲዮን ተወካዮች” ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን እንደሚያስረዱት፤ የአራት ሺህዎቹ የጉባኤው ተሳታፊዎች በአንድ አዳራሽ ታድመው ለአንድ ወር ያህል እንዲመካከሩ አይደረግም ብለዋል። አራት ሺህዎቹ ተሳታፊዎች እያንዳንዳቸው 500 አባላት ባሏቸው ስምንት ቡድኖች እንደሚከፋፈሉ ገልጸዋል። እነዚህ ስምንት ቡድኖች ኮሚሽኑ ይፋ ያደረጋቸውን ስምንት አጀንዳዎች ይከፋፈላሉ።

የትኛው አጀንዳ ለየቱ ቡድን ይሰጣል የሚለው በዕጣ ይወሰናል። 500 አባላት ያሏቸው ቡድኖች የተሰጣቸው አጀንዳ ላይ የሚወያዩት ተወካዮቹን በሌሎች አነስተኛ ቡድኖች በመከፋፈል ነው። አነስተኛዎቹ በአንጀንዳው ውይይት ካደረጉ በኋላ የደረሱበትን “የመግባባት ወይም ያለመግባባት” ምክረ ሐሳብ ይዘው 500 አባላት ወዳሉት ትልቅ ቡድን እንደሚመለሱ ፕሮፌሰር መስፍን ገልጸዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ እንደሚያስረዱት፤ ስምንቶቹ ቡድኖች በተሰጣቸው አጀንዳ ላይ በተናጠል የያዙትን አቋም በተመለከተ ከሌሎች ቡድኖች ጋር ምክክር የሚያደርጉበትም አሠራር ተዘርግቷል። ይህ የሚከናወነው ስምንቱ ቡድኖች እያንዳንዳቸው በሚወክሏቸው 25 ሰዎች ነው።

አራት መቶ የሚሆኑት እነዚህ ተወካዮች በቡድኖቹ በተናጠል ድምዳሜ “የተደረሰባቸውን ምክረ ሐሳቦች በሙሉ እንደገና ያብላሉ፣ በትነው ያያሉ” ሲሉ ፕሮፌሰር መስፍን አስረድተዋል። እነዚህ ተወካዮች በየቡድኑ የቀረቡት “ምክረ ሐሳቦች ተቀባይነት ይኖራቸዋል ወይ?” የሚለውን እንደሚመለከቱም አክለዋል።

በዚህ ደረጃ ላይ ተወካዮቹ “በጋራ የሚደርሱበት የመጨረሻ የጋራ ምክረ ሐሳብ” አራት ሺህ ተሳታፊዎች በሙሉ ለሚሳተፉበት ጉባኤ ይቀርባል። እንደ ዋና ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ በዚህ ጊዜ ሁሉም ተሳታፊዎች የሚሰበሰቡት ምክረ ሐሳቦቹን “በጋራ ለመቀበል፣ ለማፅደቅ ወይም ለመጣል” ይሆናል።

በእነዚህ ሂደቶች በሙሉ ለታሳታፊዎቹ እገዛ የሚያደርጉ “ከአመካካሪዎች”፣ “የምሁራን ቡድን” እንዲሁም ቃለ ጉባኤ መዝጋቢዎች ይኖራሉ። በዚህ ዓይነቱ ሂደት የሚለዩ “ሙሉ በሙሉ ያግባቡ” ወይም “ወደ አለመግባባት የወሰዱ ጉዳዮች በምክረ ሐሳብ ደረጃ ተሰንደው” ለመንግሥት ወይም ለሌሎች ለሚመለከታቸው “ተግባሪ” አካላት ይላካሉ።

ዋና ኮሚሽነሩ እንደሚያስረዱት በምክክር ጉባኤው መግባባት ያልደረሰባቸው ጉዳዮች “ለሕዝብ ውሳኔ” ሊቀርቡ ይችላሉ። ይህም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካኝነት ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲላክ እንደሚደረግ ጠቅሰዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን፤ ኮሚሽኑ የሚመለከታቸው አካላት ምክረ ሐሳቦቹን “በትክክል መቀበላቸውን እና ቀስ እያለ ደግሞ ወደ ትግባራ መሄዳቸውን አረጋግጦ፤ ለሕዝቡ በሚገባ ያስረዳል” ሲሉ የተቋሙን የመጨረሻው ተግባር ገልጸዋል።

“ሪፖርቶቻችንን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በቀጥታ እናደርሳለን። [የሚመለከታቸው አካላት] ‘እንሠራለን’ ብለዋል፣ ‘የተሠሩ ናቸው’፣ ‘አንሠራም ብለዋል’፤ ምክንያቱን እንዲያስረዱ ሕዝቦቻችን ይጠይቁ ወደሚለው እንሄዳለን” ብለዋል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026