Image

የሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል በወልቃይት እቅራቢያ በሚገኝ አካባቢ በፌደራል መከላከያ ሠራዊት እና በህወሓት በሚመራው የትግራይ ሠራዊት መካከል ቅዳሜ ሐምሌ 25 ቀን 2026 ዓ.ም ማለዳ ላይ ግጭት መቀስቀሱን የተለያዩ ምንጮች አመለከቱ።
 
 
አዲስ የተቀሰቀሰውን ግጭት በመጀመር ፌዴራል መንግስት የትግራይ ጊዜያዊ አስተደደርን አፍርሶ የተቆጣጠረውን ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን (ህወሓትን) ተጠያቂ አድርጓል፡፡
 
 
በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት በፌደራል መንግሥቱ የተቋቋመውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተደደርን አፍርሶ የተቆጣጠረው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መከላከያ በወልቃይት አካባቢ ሸረሪና በሚባል ስፍራ ላይ “ግልፅ ጦርነት” ከፍቷል ሲል ወንጅሏል።
 
 
የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ በፌደራል ሠራዊት እና በህወሓት ኃይሎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን ገልጸዋል።
 
ሚኒስትሩ በይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በትግርኛ ባሰፈሩት ጽሑፍ ህወሓት በሸረሪና በኩል ጦርነት አውጇል በማለት ከስሰው “ይህ ጦርነት ከወዲሁ ካልቆመ. . .የከፋ ጉዳት ይከተላል” ሲሉ አሳስበዋል።
 
 
ይህ ግጭት የተቀሰቀሰው የህወሓት መሪዎች በፌደራል መንግሥቱ የተቋቋመውን የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር አፍርሰው ሥልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላ ባለፉት ወራት በሁለቱ ወገኖች መካከል ውጥረት እየተባባሰ ከሄደ በኋላ ነው።
 
 
ሁለቱም ወገኖች ሌላ ዙር ጦርነት ለመቀስቀስ ሲካሰሱ የነበረ ሲሆን የአፍሪካ ኅብረት እና የተለያዩ አካላት ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ጥሪ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር “በየቀኑ በርካታ ውጊያ፣ ጦርነት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ትንኮሳዎች ትግራይ ውስጥ ባሉ ኃይሎች በየጊዜው ይፈጸማል” በማለት ከስሰው ነበር።
 
 
ህወሓትም በበኩሉ የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ ሌላ ዙር ጦርነት ለመክፈት ሠራዊቱን እያሰማራ መሆኑን በመጥቀስ ሲከስሱ ነበር። ባለፉት ወራት በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል እየተባባሰ በመታው ውዝግብ ምክንያት ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት በበርካቶች ዘንድ ሲስተጋባ ቆይቷል።
 
 
በ2013 ዓ.ም ተቀስቅሶ ለሁለት ዓመታት የተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት እንደጠፋበት የአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ገልጾ ነበር። የአፍሪካ ኅብረት ከሦስት ዓመት በፊት ሁለቱን ወገኖች በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ወደ ሰላም እንዲመጡ ካሸማገለ ወዲህ በክልሉ አንጻራዊ ሰላም ሰፍኖ ቆይቷል።
 
 
ሕጋዊነቱን ያጣውን ህወሓት የሚመሩት ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረ ሚካኤል ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ዳግም ጦርነት ይቀሰቀሳል ተበሎ በሚሰጋበት ወቅት ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም ለመቀሌ ነዋሪዎች ባደረጉት ንግግር የፌደራል መንግሥቱን እንደሚገዳደሩ በመግለጽ “ዛሬ እንደበፊቱ ብቻችንን አይደለንም፤ ብዙ ወዳጆች አሉን” ሲሉ ተናግረዋል።
 
 
ደብረፂዮን አክለውም “ብልጽግና ከአሁን በኋላ ትግራይን ብቻ አይገጥምም። አገዛዙን እንደ ስጋት የሚቆጥሩ ሌሎች ኃይሎች አሉ። ምንም እንኳን በራሳችን ብንተማመንም፣ ይህንን ሥርዓት ለማስወገድ የሚፈልጉ አጋሮች አሉን” ማለታቸው ተሰምቷል።
 
 
ሊቀመንበሩ አጋር ሲሉ የጠሯቸው አካላት ከአገር ውስጥ ይሁኑ ከውጭ በይፋ የጠቀሱት ነገር የለም። የፌደራል መንግሥቱ ህወሓት ከኤርትራ እና የኢትዮጵያ ተቀናቃኝ ናቸው ካላቸው አገራት ጋር በመሆን አገሪቱን የሚያናጋ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲከስስ ቆይቷል።
 
 
ህወሓት ባለፉት ወራት በትግራይ ውስጥ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ በስፋት ሲዘገብ የነበረ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶች ከምልመላው ለማምለጥ ከክልሉ እየወጡ መሆናቸውን ተነግሯል።
 
ህወሓትም በፌደራል መንግሥቱ “የኅልውና አደጋ” እንደተደቀነበት በመግለጽ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በይፋ በመግለጫ እና በመገናኛ ብዙኃን ሲገልጽ ቆይቷል።
 
 
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በትግራይ ክልል የተካሄዱት ሕዝባዊ ስብሰባዎች እና መግለጫዎች ከፌዴራል መንግሥት ጋር ያለውን ውጥረት ሊያባብሱና ሁኔታውን ወደ ጦርነት ሊገፉ ይችላሉ የሚል ስጋት ፈጥረዋል።
 
 
‘እምቢኝ ለብሔር እልቂት’ በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ከተሞች እየተካሄዱ ያሉት እነዚህ ስብሰባዎች የሚመሩት በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ነው። በክልሉ እነዚህ ስብሰባዎች በዘመቻ መልክ እየተካሄዱ የሚገኙት በህወሓት እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት እየተካረረ በመጣበት ወቅት ነው።
 
 
አንዳንድ ታዛቢዎች የህወሓት መግለጫዎች እና ስብሰባዎች ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር ያለውን ውጥረት ወደ ሌላ ጽንፍ የሚያሸጋግሩ ይሆናሉ ብለው ይፈራሉ። ሌሎች ደግሞ ከነዋሪዎች ጋር መመካከር አዎንታዊ ውጤት ሊያስገኝ እና ወደ መፍትሄ ሊያመራ እንደሚችል ተስፋ ያደርጋሉ።
 
 
በካናዳ ካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትን ፕሮፌሰር ጌታቸው አሰፋ “በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ ጦርነት እንደተቃረብን እንደሆነ ይሰማኛል” ሲሉ ለቢቢሲ መናገራቸው ይታወሳል።
 
 
የህወሓት መሪዎች በሚሰጡት መግለጫዎች እና ንግግሮች ውስጥ “በጄኖሳይዳል ስርአት መቃብር ላይ” የሚለውን ሐረግ መጠቀማቸው እንዲሁም ከዚህ በፊት በነበረው ጦርነት ልጆቻቸውን ያጡ ቤተሰቦች የቀሩ ልጆቻቸውን ለጦርነት እንዲያቀርቡ የሚያሳምን እና ሚገፋፋ ይመስላል ብለዋል።
 
 
በሌላ በኩል ደግሞ ባለፉት ሁለት ወይም ሦስት ቀናት ውስጥ ከማዕከላዊው መንግሥት ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ መከፈቱን አስተውያለው ይላሉ። “ስለዚህ የመጨረሻ የሚመስል ሁኔታን እየተመለከትን ነው፤ ነገር ግን ምናልባት [ጦርነት የሚቀርበት] ዕድል የለም ማለት አልፈልግም” ብለዋል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026