Image

የመከላከያ ጄኔራሎችን ለፖሊስ አዛዥነት መሾም ምን ያመለክታል?

እየተገባደደ በሚገኘው በ2018 ዓ.ም የመከላከያ ጄኔራል መኮንኖች ከጦር ሠራዊት አዛዥነት ወደ ፖሊስ አዛዥነት ተዛውረው እንዲሾሙ ተደርገዋል፡፡ በትናንትናው እለት የቀድሞው የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አሚሶም) አዛዥ ሌተናንት ጄነራል ጥጋቡ ይልማ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ላለፈው አንድ ዓመት ከአምስት ወራት ገደማ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው የሰሩት ዶ/ር ዘላለም መንግሥቴ ወደ ቀድሞ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ኃላፊነታቸው እንደተመለሱ ተገልጿል።

አዲሱን አዛዥ ሌተናንት ጄነራል ጥጋቡን የሾሙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ መሆናቸውን የክልሉ ፖሊስ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል። ከስድስት ወራት በፊት መጋቢት 2/2018 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመከላከያ የምድር ኃይል ዋና አዛዥ የነበሩትን ሌተናንት ጄነራል አስራት ደኔሮን የአዲስ አበባ ፖሊስን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ መሾማቸው ይታወሳል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው ሌ/ኮሎኔል ይልማ ካሳሁን የተባሉ የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባል እንደገለጹት እንዲህ ያለው ዝውውር ከአጼ ኃ/ሥላሴ ዘመን ጀምሮ ሲተገበር መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡ በተለይ በወታደራዊው መንግስት ጊዜ ተመሳሳይ የሹመት ዝውውሮች መካሄዳቸውን አስረድተዋል፡፡

እንደ ኮሎኔል ይልማ ገለጻ የመከላከያ ጄኔራሎችን በፖሊስ አዛዥነት መሾም በሀገር ላይ እንዳለው ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ፣ የፖለቲካ ሥርዓት እና በወቅቱ እንዳለው የፀጥታ ሁኔታ የተለያየ ትርጉምና አመላካችነት ሊኖረው ይችላል። ይህ ዓይነቱ ውሳኔ በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ ጎኑ የሚታይ ይሆናል ብለዋል፡፡

በአንድ በኩል የፀጥና የደህንነት ስጋቶችን በጠንካራ እጅ ለመቆጣጠር በመፈለግ ሲሆን ይኸውም በሀገር ውስጥ ከፍተኛ የጸጥታ መበላሸት፣ የሽብርተኝነት ስጋት፣ ወይም የታጠቁ አማፂያን ሲኖሩ መንግሥት ጠንካራ ወታደራዊ ልምድ ያላቸውን መሪዎች ወደ ፖሊስ እንደሚያመጣ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ወታደራዊ ስልትን በመጠቀም የመከላከያ ጄኔራሎች የለመዱትን ወታደራዊ የዕዝ ሰንሰለት እና የጥቃት መከላከል ስልት በፖሊስ መዋቅር ውስጥ በመተግበር ሰላምን በፍጥነት ለማስከበር ዓላማ ሊኖረው ይችላል።

በአጠቃላይ፣ ይህ እርምጃ መንግሥት ለሲቪል ደህንነትና ለሕግ የበላይነት ከመደበኛው የፖሊስ አሠራር ይልቅ ለድንገተኛና ለጠንካራ ወታደራዊ መፍትሔዎች ቅድሚያ መስጠቱን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል በማለት ኮሎኔል ይልማ አስረድተዋል፡፡

ላለፉት ሦስት ዓመታት ደም አፋሳሽ ግጭት ውስጥ የሚገኘውን የአማራ ክልል የፖሊስ ኃይል የመምራት ኃላፊነትን የተረከቡት ሌተናንት ጄነራል ጥጋቡ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከ40 ዓመት በላይ ልምድ ያላቸው ወታደራዊ መኮንን ናቸው።

ሌተናንት ጄነራል ጥጋቡ ይህንን ኃላፊነት የተረከቡት፣ መንግሥት በክልሉ የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ኃይሎች “ጽምዶ” በሚል በሚጠራው ጥምረት አማካኝነት ከትግራይ ኃይሎች ጋር ትብብር መፍጠራቸውን እየገለጸ ባለበት ወቅት ነው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የተባለውን ታጣቂ ቡድን የሚመሩት ዘመነ ካሴ ‘ሌ ቴምፕስ’ ለተባለው የሲውዘርላንድ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ የትግራይ ኃይሎችን ጨምሮ ከሌሎች ታጣቂዎች ጋር ለመተባባር “ለስምት ወራት ገደማ” ውይይት መደረጉን ተናግረዋል። የትብብሩ አካል ተብለው ከተጠቀሱት መካከል “የጉሙዝ፣ በርታ፣ ሶማሊ እና ኦሮሞ ኃይሎች” ይገኙበታል።

በክልሉ የታጣቂዎችን እንቅስቃሴ ለመግታት የሚደረገው ጥረት በዋነኛነት በመከላከያ ሠራዊት የሚመራ ሲሆን፣ በክልሉ ፖሊስ ሥር የሚገኙት የአድማ ብተና ኃይሎችም ተሳትፎ ያደርጋሉ።

አዲሱ የክልሉ ፖሊስ አዛዥ ወደዚህ ኃላፊነት ከምጣታቸው አስቀድሞ የመከላከያ ሠራዊቱ ጤና ዋና መምሪያን በኃላፊነት እየመሩ ነበር። የመከላከያ የሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ እና የመከላከያ ካውንስል አባል በመሆንም አገልግለዋል።

ሌተናንት ጄነራል ጥጋቡ ከአገር ውስጥ በተጨማሪ በቀጣናዊ የመከላከያ ሠራዊት ስምሪት ላይ በአመራርነት ሰርተዋል። ከየካቲት 2011 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 2012 ድረስ አልሸባብ ሶማሊያ ላይ የደቀነውን ስጋት ለመቀነስ በተባበሩት መንግሥታት ድጋፍ የተቋቋመውን የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) በአዛዥነት መርተዋል።

ከመጋቢት 1999 ዓ.ም አንስቶ ለአስራ አምስት ዓመታት የቆየው ይህ ተልዕኮ፣ መጋቢት 2014 ዓ.ም የቆይታ ጊዜውን አጠናቅቆ፣ በአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) መተካቱ ይታወሳል።

ይህ የሽግግር ተልዕኮም ከ2017 ጥር ጀምሮ ‘አውሶም’ በተባለው የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ መተካቱ ይታወሳል። አውሶም በመጪው ታኅሳስ ወር የቆይታ ጊዜው ያበቃል።

ለዚህ ተልዕኮ ወታደር የሚያዋጡ አገራት ባለፈው ሐምሌ ላም በዩጋንዳ ካምፓላ ውስጥ ባካሄዱት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙት አዛዥ ሌተናንት ጄነራል ጥጋቡ ነበሩ። ሌተናንት ጄነራል ጥጋቡ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በፖሊስ አዛዥነት የተሾሙ ሁለተኛው ወታደራዊ መኮንን ናቸው።

ባለፈው መጋቢት የመከላከያ የምድር ኃይል ዋና አዛዥ እንዲሁም የሠራዊቱ መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ሌተናንት ጄነራል አስራት ደኔሮ የአዲስ አበባ ፖሊስን እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሾማቸው ይታወሳል።

ከመጋቢት 2017 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው የቆዩት ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግሥቴ፣ ከዚህ ቀደም ወደ ነበሩበት የፌደራል ፖሊስ ምክትል ዋና ኮሚሽነርነት ኃላፊነት መመለሳቸውን የክልሉ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026