Image

አሜሪካ ከአምስት ዓመታት በፊት በትግራይ ውስጥ ከተካሄደው ጦርነት ጋር ተያይዞ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ዘመን በሁለቱ አገራት ወታደራዊ፣ የፖለቲካ እና ሌሎች ተቋማት አመራሮች እንዲሁም ተቋማት ላይ የተለያዩ ዓይነት ዕቀባዎችን መጣሏ የሚታወቅ ነው፡፡

የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መነሳቱን ተግባራዊ ሲያደርግ፣ በኤርትራ የመከላከያ ኃይል እና ሌሎች ተቋማት ላይ የጣለውን ማዕቀብ ማንሳቱን አስታውቋል።

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገር መከላከያ ንግድ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የቆየው የጦር መሳሪያ እንደሚነሳ ካሳወቀ በኋላ ውሳኔው ከመስከረም 8/2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑን ይፋ ሆኗል።

ዳይሬክቶሬቱ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ስትከተል የነበረችውን የክልከላ ፖሊሲ በማንሳት አሁን ላይ በዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ ዝውውር ደንብ ቁጥጥር የሚደረግባቸውን እና ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዙ የፈቃድ ማመልከቻዎችን ሲገምግም ቆይቶ ነው የዕገዳው መነሳት ተግባራዊ የሆነው።

በዚህም በኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የነበረው የጦር መሳሪያ ሽያጭ ዕቀባ መነሳቱን የሚያሳውቅ ደንብ መስከረም 8/2019 ዓ.ም ይፋ ሆኖ፣ ኢትዮጵያ በአሜሪካ የዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ዝውውር ክልከላ ደንብ ዝርዝር ውስጥ ከሚገኙ አገራት ተርታ “እንድትሰረዝ” መደረጓ ተገልጿ።

በዚህም ኢትዮጵያ ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለፖሊስ፣ ለደኅንነት እና ለሌሎችም የአገር ውስጥ የደኅነንት ኃይሎቿ የሚውሉ የመከላከያ ቁሳቁሶችን እና አገልግሎቶችን ከውጭ ገዝታ ማስገባትም ሆነ ወደ ውጭ አገራት መላክ እንድትችል የሚፈቅድ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የትራምፕ አስተዳደር በኤርትራ የመከላከያ ኃይሎች እና በሌሎች አካላት ላይም ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ አንስቷል። ኤርትራ ለሁለት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ከነበራት ተሳትፎ ጋር በተያያዘ በ2014 ዓ.ም በኤርትራ ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ ማዕቀቦች ጥላ ቆይታለች።

በዚህም የአሜሪካ መንግሥት በኤርትራ ገዢ ፓርቲ ህዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ (ህግዴፍ) እንዲሁም ከፓርቲው ጋር ትስስር ባላቸው ህድሪ ትረስት እና ሬድ ሲ ትሬዲንግ ኮርፖሬሽን ላይ ማዕቀብ ጥሏል። በተጨማሪም በኤርትራ መከላከያ ኃይል እና በሁለት ከፍተኛ የኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ ዕቀባ ተጥሎ ነበር።

በትግራይ ክልል ለሁለት ዓመት የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከአንድ ዓመት በኋላ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መስከረም 7/2014 ዓ.ም ላይ በጦርነቱ ውስጥ ዋነኛ ተዋንያን በነበሩት ኃይሎች መሪዎች እና ተቋማት ላይ የተለያዩ ዕቀባዎች እንዲጣል የሚያደርግ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ አውጥተው ነበር።

ከእነዚህም መካከል ግንባር ፈጥረው የትግራይ ኃይሎችን ሲወጉ በነበሩት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መንግሥታት ባለሥልጣናት እና ተቋማቶቸቻው ላይ ማዕቀቦት ተጥለው ለአምስት ዓመታት ከቆዩ በኋላ ነው እንዲነሳ መወሰኑ የተገለጻው።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከተመለሱ በኋላ አሜሪካ ከሁለቱ አገራት መሪዎች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል እንደምትፈልግ ሲገለጽ የነበረ ሲሆን የተለያዩ ግንኙነቶች መደረጋቸው ሲዘገብ ቆይቷል።

ማዕቀቡ መነሳቱ የተገለጸው በትግራዩ ጦርነት ወቅት አጋር የነበሩት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት ግንኙነት ተበላሽቶ ወደ ጦርነት ይገባሉ እየተባለ ባለበት ጊዜ ነው።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026