Image

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ ተገንጣዮቹ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) እና ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓትን) ጨምሮ ሰባት ታጣቂ ቡድኖችና የመገንጠል አላማ ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች “የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና” የተሰኘ ፀረ-መንግሥት ጥምረት መመሥረታቸውን መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ አውጀዋል።

 

 

 

ይህ ጥምረት ምን ያህል ሊጓዝ ይችላል? ለሚለው ጥያቄ የፖለቲካና የወታደራዊ ጉዳዮች ተንታኞች ነባራዊ ሁኔታዎች ከሚያሳዩዋቸው ዕድሎችና ተግዳሮቶች አንጻር ትንታኔ ሰጥተውባቸዋል፡፡

 

 

እንደተንታኞቹ ገለጻበጥምረቱ ውስጥ የተካተቱት ኃይሎች በተለይም የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የአማራ ፋኖ እና ህወሓት ለዓመታት እርስ በርሳቸው ሲዋጉና ጥብቅ የፖለቲካና የርዕዮተ-ዓለም ቅራኔ የነበራቸው ናቸው።

ለምሳሌ ፋኖ በትግራዩ ጦርነት ወቅት ከመንግሥት ጎን ተሰልፎ ህወሓትን ሲዋጋ የነበረ ሲሆን፣ እንደ ወልቃይትና ራያ ያሉት የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች አሁንም በፋኖ እና በህወሓት መካከል ያልተፈቱ ትልልቅ የደምና የፖለቲካ ጉዳዮች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ጥልቅ የዓላማ ልዩነት ጥምረቱ በዘላቂነት አብሮ ለመጓዝ ያለውን ዕድል ጥያቄ ምልክት ውስጥ ሊከተው እንደሚችል አመልክተዋል።

ጥምረቱ በመንግሥት ላይ ከፍተኛ የደኅንነትና ወታደራዊ ውጥረት ሊፈጥርና የመንግሥትን ኃይል ለመፈታተን ቢችል እንኳን፤ ቡድኖቹ በመካከላቸው ያለውን የታሪክ፣ የርዕዮተ-ዓለም እና የይገባኛል ጥያቄ ቅራኔዎችን በውይይት መፍታት ካልቻሉ ጥምረቱ ረጅም ርቀት የመጓዝ ዕድሉ ጠባብ መሆኑንና አልፎ ተርፎም ወደ አዲስ የእርስ በርስ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይገምታሉ።

ቡድኖቹ ከመንግሥት ከመንግስት ጋር የመደራደር አቅም ቢያገኙ እንኳን በቀጣይ ስለሚኖረው የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታና መዋቅር ግልጽና ወጥ የሆነ የጋራ ራዕይ ስለሌላቸው፣ ሕዝቡ ጥምረቱን በጥርጣሬ ሊመለከተው ይችላል። መንግሥትም ጥምረቱን እንደ አንድ የመደራደር አቅም ያለው ጠንካራ ስብስብ ሳይሆን “የሽፍቶችና የጥፋት ኃይሎች ስብስብ” በማለት እየገለጸው ይገኛል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር  የሆነው ዘመነ ካሴ በትግራይ መገናኛ ብዙኀን ላይ ባነበቡት መግለጫ መሠረት ትብብሩ ህወሓትን፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን እና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄን ጨምሮ ሰባት ታጣቂ ቡድኖችን ያካተተ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ዘመነ ካሴ በመግለጫው ይህንን ይበል እንጂ የፋኖ አመራሮች ቀደም የህልውና ጦርነት ውስጥ ገብተናል ያሉበትን ምክንያት ሲያብራሩ በኦሮሚያ በተለይ በወለጋ ውስጥ የሚኖረው የአማራ ህዝብ በኦነግ ሠራዊት በመጨፍጨፉ ምክንያት ህዝቡን በህይወት የመኖር መብት ለማረጋገጥ ትጥቅ አንስተው ውጊያ መጀመራውን ሲናገሩ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ፈጽሟል ካሉት ተገንጣይ ቡድን ጋር ጥምረት መፈጸማቸውን ሲናገሩ እርስ በርሱ ለተቃረነው ድርጊታቸው ጥያቄ ይነሳብኛል እንኳን አላሉም፡፡

በትናንትናው ዕለት ይፋ በሆነው ትብብር አፋብን፣ ህወሓት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ፣ የጉሙዝ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ የኦጋዴን ሕዝብ ነፃነት ግንባርና የአፋር ብሄራዊ አንድነት ግንባር አባላት መሆናቸው ተነግሯል።

በጠላትነት በሚተያዩትና የርዕዮተ-ዓለምም ሆነ የአላማ አንድነት በሌላቸው ቡድኖች መካከል የተመሠረተው ይህ ጥምረት “የሕዝቦችን ኅልውና እና የአገርን ደኅንነት መታደግ” ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል።

“ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን ማረጋጋት፣ ከጎረቤት አገር ጋር ያለውን ግንኙነት ማሻሻል እና የአገሪቱን ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ቁመና ማስተካከል” የሚሉትም በመጀመሪያው ዋነኛ ዓላማቸው ሥር መካተታቸው ተመልክቷል።

ትብብር ለኅልውና በሁለተኛ ዋና ዓላማነት በመግለጫው የጠቀሰው ጉዳይ፤ “ሕዝባዊ እና ሕገ መንግስታዊ ውይይት” ማድረግን ነው። ለኢትዮጵያ “ሰላም” እና “ለሕዝቦች ቀጣይ ኅልውና” ሲባል እንደሚደረግ የተገለጸው ይህ ውይይት፤ “ሀቀኛ፣ ታማኝ፣ ሁሉንም ያካተተ እና ያሳተፈ” እንደሚሆን በመግለጫው ላይ ተመልክቷል።

የውይይቱ ዓላማም “ወሳኝ ሕዝባዊ እና አገራዊ ጥያቄዎችን በሕዝቦች ቀጥተኛ ተሳትፎ መመለስ” እንደሆነም አቶ ዘመነ በመግለጫቸው አብራርተዋል።

የትብብሩ መመስረት ይፋ የተደረገው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች ከኤርትራ ጋር “ጽምዶ” መመስረታቸው ይፋ ከተደረገ ከወራት በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሐምሌ ወር ለፓርላማ አባላት ኢትዮጵያ “የመከላከል አቅም” ላይ እንደሚተማመኑ ተናግረው ነበር።

“ሌሎች ቢጨመሩም እንኳ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚሰማን ፍርሃት የለም” ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም አቶ ዘመነ ካሴ የሚመሩት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) እንቅስቃሴው “በአማራ ክልል ብቻ የተወሰነ እንዳልሆነ” ለቢቢሲ ገልጾ ነበር።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በበኩሉ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት በሰጠው መግለጫ የፋኖ አመራሮች በኦሮሚያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ እና ራሳቸውን ፋኖ ብለው ከሚጠሩ አካላት እንዲያርቁ ጠይቋል።

ሠራዊቱ በመግለጫው “ከእንደዚህ ዓይነት ቡድን ጋር በመተባበር፣ ሊገኝ ከሚችለው የአጭር ጊዜ ወታደራዊ ጥቅም እጅግ የላቀ የፖለቲካ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል አደጋ” እንዳለው ገልጾ፣ የአማራ ኃይሎች ይህን ቡድን በተመለከተ የሚያደርጉትን “ኃላፊነት ከጎደለው የሚዲያ ንግግሮች እንዲታቀቡ እና ከዚህ ቡድን ጋር ያላቸውን ግንኙንት በግልጽ እንዲያቋርጡ” ጠይቆ ነበር።

የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ደግሞ ለፐልስ ኦፍ አፍሪካ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደ ፋኖ፣ ኦነግ ሸኔ እና ህወሓት ያሉ አካላት የኤርትራን ዓላማ ለማሳካት እና የጦርነቱን ሸክም እንዲሸከሙ ተሰልፈዋል ሲሉ ከስሰዋል።

አቶ ጌታቸው ለመገናኛ ብዙኃኑ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ የኤርትራ መንግሥት ከግብፅ ጋር በመሆን የምሥራቅ አፍሪካን ሰላም ለማናጋት እና ቀጣናውን ለማተራመስ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ህወሓት እና የኤርትራ መንግሥት አብረው መሠለፋቸው እጅግ አደገኛና የትግራይንና የአማራን ሕዝብ ለከፋ ሁኔታ የሚዳርግ መሆኑን አቶ ጌታቸው ጨምረው አስረድተዋል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026