Image

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በደብዳቤ አሳወቁ፡፡

ዶ/ር ጌዲዮን ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት በጻፉት ደብዳቤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ደብዳቤውን የጻፈችው በትግራይ ጦርነት ዳግም ከተጀመረ ከሁለት ሳምንት በኋላ ረቡዕ ዕለት መስከረም 27/2019 ዓ.ም የኤርትራ ወታደሮች በብዛት በተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች መታየታቸው በስፋት ከተዘገበ በኋላ ነው።

ቢቢሲን ጨምሮ የተለያዩ የዜና ምንጮች የኤርትራ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባታቸውን በተመለከተ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርገው ቢዘግቡም፣ ኤርትራ ግን ኢትዮጵያ ልትከፍተው ለምትፈልገው ወረራ ሰበብ እየፈለገች ነው በማለት ክሱን ውድቅ አድርጋዋለች።

በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜም ኤርትራ አስቀድማ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ ባድሜን እና ጾረናን በመውረር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሜካናይዝድ ጦር በአካባቢው ላይ ካሰፈረች በኋላ “ኢትዮጵያ ድንበሬን አልፋ ልትወጋኝ ነው” የሚል የድረሱልኝ ጥሪ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሰማቷ ወረራው በጦርነት እስከሚቀለበስ ድረስ እውነታውን ለመለየት አስቸጋሪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ኤርትራ ጦሯን አስቀድማ ኢትዮጵያ ውስጥ አስገብታ መሬት እንዲይዝ በማድረጓ ወረራውን ለመቀልበስ ጦርነት የተካሄደው በአብዛኛው በኢትዮጰያ ግዛት ውስጥ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ሰላማዊ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ለአካል ጉዳትና ለመፈናቀል ተዳርገዋል፡፡

የኤርትራ ሠራዊት በጦርነት ተሸንፎ ከኢትዮጵያ መሬት እንዲወጣ ከተደረገ በኋላም የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ወደ መሬታቸው ለመመለስ በተቀበሩ ፈነጂዎች ምክንያት አስቸጋሪ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በወረራው ይህንን ሁሉ ዋጋ ከፍላ ከኤርራ የተከፈላጥ ካሳ እንኳን አልነበረም፡፡

አሁንም ኤርትራ በድጋሚ ወረራ ፈፅማለች፤ ሆኖም ግን ከድርጊቷ እንድትቆጠብና ሠራዊቷን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ እንድታስወጣ የገሰጻት ዓለም አቀፍ ተቋም እስካሁን አልታየም፡፡ በትግራይ በኩል ድንበር ጥሶ የገባው ሠራዊት አዲግራትንና ዛላንበሳን ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡

ቢቢሲ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጭ እንደተረዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን በጻፉት ደብዳቤ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ለፀጥታው ምክር ቤት አባላት በላከችው ደብዳቤ “ኤርትራ በተደጋጋሚ በፈጸመችው ጸብ አጫሪነት እና ድንበር ጥሶ የመግባት እርምጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ መደቀኑን” በመጥቀስ ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቃቸውን አስታውሰዋል።

“ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን በመጣስ ወረራ ፈጽማለች፣ ኢትዮጵያ ደግሞ የወረራው ሰለባ ናት” በማለትም ከስሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን በደብዳቤያቸው ኤርትራ የፀብ አጫሪነት ድርጊቷን በአሁኑ ጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግራ “ሜካናይዝድ ክፍሎችን ጨምሮ ወታደሮቿን በጥልቀት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አሰማርታለች። ይህም ሦስት የትግራይ ዞኖችን በማካተት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ30 አስከ 60 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ርቀት ወደ ውስጥ ገብተዋል” ብለዋል።

ሚኒስትሩ የኤርትራ ድርጊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ውስጥ የሰፈሩትን መሠረታዊ መርሆዎች በግልጽ የሚጥስ ነው በማለት “ይህም ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ሕጋዊ መብት እንድትጠቀም የሚያስገድድ ነው” ሲሉ ጽፈዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለፀጥታው ምክር ቤት በጻፉት ደብዳቤ ተፈጸመ ያሉትን ወረራ ከማሳወቅ ባለፈ አገራቸው ለምትወስደው የመከላከል እርምጃ ድጋፍም ጠይቀዋል። “በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም” በማለት ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የገጠማትን ሁኔታ በመረዳት ድጋፍ እንዲደያርግላት እና ከጎኗ እንዲቆም ጠይቀዋል።

ሚኒስትሩ በደብዳቤያቸው ኢትዮጵያ ከኤርትራ በኩል ለረዥም ጊዜ ሲፈጸሙ ለነበሩ ትንኮሳዎች በትዕግሥት እና ራስን በመቆጠብ መቆየቷን አመልክተዋል።

ስለዚህም “ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም። ኤርትራ ወራሪ ናት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የወረራ ሰለባ ናት። ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እየጣሰች ነው” ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከ25 ዓመታት በፊት በድንበር ይገባኛል ሰበብ ለሁለት ዓመታት ደም አፋሳሽ ጦርነት ካደረጉ በኋላ ከስምንት ዓመት በፊት ግንኙነታቸው ቢታደስም በትግራይ የተካሄደው ጦርነት ካበቃ በኋላ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት በተለይ ኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎቷን ካስታወቀች በኋላ ውዝግቡ የበረታ ሲሆን ወደ ግጭት ይገባሉ ተብሎ ሲነገር ቆይቷል። ከሁለት ሳምንት በፊት የፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት ከህወሓት ኃይሎች ጋር በአማራ እና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ስፍራዎች ላይ ወደ ግጭት ከገቡ በኋላ የኤርትራ ኃይሎች በግጭቶቹ ተሳታፊ ናቸው የሚል ክስ ቢቀርብም ኤርትራ ስታስተባብል ቆይታለች።

የኤርትራ ሠራዊት በብዛት ወደ ትግራይ ክለል ዘልቀው መግባታቸውን ነዋሪዎች መግለጻቸውን ተከትሎ ለወጡት ዘገባዎች የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በሰጡት ምላሽ “ኢትዮጵያ በጎረቤቷ ላይ ጦርነት ለመክፈት የምታደርገው ጥረት አካል ነው” ሲሉ አጣጥለውታል።

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

እንግሊዝ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ እንደምትገድብ አስጠነቀቀች

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና…

ጥቅም 15, 2026
ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
የኤርትራ ወታደሮች አፋር ክልል ገብተው ውጊያ ከፈቱ

የኤርትራ ወታደሮች አፋር ክልል ገብተው ውጊያ ከፈቱ

የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በመግባት ከህወሓት ታጣቂዎች ጎን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው ሲል የአፋር ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡ የአፋር ክልል…

ጥቅም 1, 2026