Image

ሻዕቢያን ከሳህል በረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ጀምሮ ኤርትራን ገንጥሎ መንግስት እስከሚሆን ድረስ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አጋር ሆነው የፋይናስና የሎጀስቲክ ድጋፍ እዚህ ደረጃ ላይ ቢያደርሱትም የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የለየለት አምባገነንተት እየከፋ በመምጣቱ ወዳጆቹ ሁሉ እየራቁት ብቻውን ቀርቷል፡፡
 
የዩኬ መንግሥት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የኤርትራ ባለሥልጣናት ስደተኞችን ለመመለስ ለመተባበር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከስሷል። እንግሊዝ አሁን ላይ እጥለዋለሁ ያለችው ክልከላም የኤርትራ ዲፕሎማቶች ያለፈቃድ ከለንደን ከ60 ኪሎሜትር ርቀት በላይ እንዳይንቀሳቀሱ ያግዳል። ይህ በኤርትራ መዲና አስመራ ያሉ የብሪታኒያ ባለሥልጣናት ላይ የተጣለው ክልከላ ነጸብራቅ እንደሆነም የአገር ውስጥ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
 
 
በዩኬ የጥገኝነት ጥያቄ ሥርዓት ላይ ለውጥ መደረጉ ሲገለጽ፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሯ፣ ሕገ ወጥ ስደተኞችን ለመመለስ ለማይተባበሩ አገራት የቪዛ ክልከላ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸው ነበር።
 
 
እንደ የአገር ውስጥ ጉዳይ ቢሮ መረጃ ከሆነ ከአውሮፓውያኑ 2026 መጀመሪያ ወዲህ ከ20 ሺህ 400 በላይ ስደተኞች በአነስተኛ ጀልባዎች ወደ ዩኬ ገብተዋል። ይህ ቁጥር ከቀደመው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 40 በመቶ ቀንሷል።
 
 
ከሐምሌ 2025 እስከ ሰኔ 2026 ድረስ ባሉት ወራትም ወደየአገራቸው የተባረሩ እና የተመለሱ ስደተኞች ቁጥር ከ40 ሺህ 600 በላይ ነበሩ። ይህም በቀደመው ዓመት ከነበረው በ8 በመቶ ጨምሯል። ከተመላሾቹ መካከል ከ6 ሺህ የሚያንሱት በወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ የተባሉ ናቸው።
 
 
ዩናይትድ ኪንግደም ስደተኞች ወደ አገራቸው ከሚመለሱበት ፖሊሲ ጋር በተያያዘ ኤርትራውያን ወደ አገሪቷ እንዳይገቡ እገዳ ለመጣል ዛተች። የዩኬ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሻባና ማሕሙድ፣ የኤርትራ መንግሥት በትናንሽ ጀልባዎች የገቡ እና ወንጀል የፈፀሙ ስደተኞችን ካልተቀበለ ኤርትራውያን ወደ አገሪቷ እንዳይገቡ እንደሚከለክሉ አስታውቀዋል።
 
 
ከዚህም በተጨማሪ ከመጪው ሐሙስ ጀምሮ የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከለንደን ውጪ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ እንደሚጣልባቸው ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ለቪአይፒ ሰዎች የሚደረገው ፈጣን የቪዛ አገልግሎትም ይቆማል ብለዋል።
 
 
ከዚህ ቀደም ሚኒስትሮች የቪዛ ክልከላ እንደሚጥሉ በማስፈራራት ሌሎች አገራትም ተመላሽ ስደተኞችን እንዲቀበሉጫና ሲያሳድሩ ነበር። በርካታ ስደተኞች በአነስተኛ ጀልባዎች ወደ ዩኬ የሚገቡ ሲሆን እስከ ሰኔ ባሉት 12 ወራት ውስጥ ወደ አገሪቱ ከገቡ ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ የኤርትራ ዜጎች ናቸው። በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አገሪቷ ከሚገቡት ስደተኞች ውስጥም 18 በመቶ የሚሆኑትን ይይዛሉ።
 
 
ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ በለንደን የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲን ቢጠይቅም ምላሽ አላገኘም። “ኤርትራ ወንጀለኞችን እና በዩኬ ለመቆየት ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸውን ዜጎችን ለመቀበል ሁሉም እድል ነበራት፤ ነገር ግን እንደሌሎች አገራት ፈቃደኛ አልሆነችም” ብለዋል የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሯ።
 
 
በመሆኑም ለመተባበር ፈቃደኛ ባልሆኑ ሌሎች አገራትም ላይ ተጨማሪ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንደማያመነቱ አክለዋል።በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ዩኬ በአንጎላ፣ ናሚቢያ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ላይ ተመሳሳይ እገዳ እንደምትጥል አስታውቃ ነበር።
 
 
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ላይ ክልከላ ተጥሎ የነበረ ሲሆን ስደተኞችን ለመቀበል የምታሳየው ትብብር በመሻሻሉ እገዳው መነሳቱን የአገር ውስጥ ጉዳይ ቢሮው አስታውሷል። አንጎላ እና ናሚቢያም ክልከላው ከመጣሉ በፊት ተመላሽ ስደተኞችን ለመቀበል ተስማምተዋል።
 
የእንግሊዝ (ዩናይትድ ኪንግደም) መንግስት የኤርትራን መንግስት አስመልክቶ ከያዛቸው ዋና ዋና ዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካዊ አቋሞች አንዱና ዋናው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል እየበረታ የመጣውን የድንበር ውጥረት ተከትሎ፣ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ፣ የኮመንዌልዝ እና ልማት መስሪያ ቤት ሁሉም ወገኖች የወሰን ሉዓላዊነትን እና የግዛት አንድነትን እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።
 
ማናቸውም ወገን የጎረቤት ሀገርን ድንበር የሚጥስ ተግባር እንዲያቆም እና ወደ ውይይት እንዲመለስም በጥብቅ አሳስቧል። እንግሊዝ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ላይ በተደጋጋሚ እንደገለጸችው፣ በኤርትራ ያለውን ፍጻሜ የሌለው ያልተገደበ የብሔራዊ አገልግሎት (ወታደራዊ ግዳጅ) አጥብቃ ትቃወማለች። ይህ ስርዓት የዜጎችን ህይወት እያጠፋና ለስደት እየዳረገ መሆኑን በመጥቀስ ማሻሻያ እንዲደረግበት ትጠይቃለች።
 
የኤርትራ መንግስት በፖለቲካ እና በሃይማኖት ምክንያት ያለፍርድ ያሰራቸውን በርካታ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት መርማሪዎች ጋር እንዲተባበር የእንግሊዝ መንግስት ግፊት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
 
እ.አ.አ. በኦክቶበር 2026 የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ የእንግሊዝ መንግስት የኤርትራ መንግስት በትናንሽ ጀልባዎች የመጡ ስደተኞችን እና የወንጀል ድርጊት ፈጽመው የተፈረደባቸውን ዜጎቹን በስምምነት መልሶ ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ማንኛውም የኤርትራ ዜጋ ወደ እንግሊዝ እንዳይገባ ሙሉ የቪዛ እገዳ ለመጣል አስገዳጅ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። በተጨማሪም በለንደን የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከለንደን ውጭ እንዳይንቀሳቀሱ የጉዞ ገደብ ጥሏል።

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

ኦነግ ለኢሳይያስ ንግግር በመግለጫ ምላሽ ሰጠ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ትናንት ባወጣው መግለጫ “ህዝባችን ላይ የታወጀና በቀጣናው ደግሞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየጠነከሩ በመምጣታቸው እንዲሁም…

ጥቅም 14, 2026
የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የተቋረጠው የትግራይ በረራ በድጋሚ መጀመሩ ምን ያመለክታል?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ…

ጥቅም 12, 2026
ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

ኢትዮጵያ ስለተፈጸመባት ወረራ ለተመድ የፀጥታ ም/ቤት አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት…

ጥቅም 12, 2026
የኤርትራ ወታደሮች አፋር ክልል ገብተው ውጊያ ከፈቱ

የኤርትራ ወታደሮች አፋር ክልል ገብተው ውጊያ ከፈቱ

የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በመግባት ከህወሓት ታጣቂዎች ጎን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው ሲል የአፋር ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡ የአፋር ክልል…

ጥቅም 1, 2026